ኤስኢኦ (SEO) ምንድንነው?
ዲጂታል ማርኬቲንግ በሁለት አበይት ክፍሎች የሚከፈል መስክ ነው። እነርሱም የክፍያ ዲጂታል ማርኬቲንግ(Paid digital marketing) እና ኦርጋኒክ ዲጂታል ማርኬቲንግ ይባላሉ። የክፍያ ዲጂታል ማርኬቲንግ ማለት በዲጂታሉ ዓለም የሚሰሯቸውን ማስታወቂያዎች ለድረ ገፆች በመክፈል ለተጠቃሚዎች እንዲደርሱ የሚያደርጉበት የማርኬቲንግ መንገድ ሲሆን ፤ ተፈጥሯዊ ዲጂታል ማርኬቲንግ (Organic digital marketing) ደግሞ የተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም ያለምንም ክፍያ በዲጂታል አማራጮች መልዕክት የሚያስተላልፉበት መንገድ ነው። […]