digital marketing for banks

ዲጂታል ማርኬቲንግ ለባንኮች (ክፍል ሁለት)

በመጀመሪያው ክፍል ፅሑፋችን ባንኮች እና የፋይናንስ ተቋማት ወደሰፊው የዲጂታል ማርኬቲንግ ዓለም በመቀላቀል የተቋማቸውን ብራንድ ስለማሳደግ ትኩረት ሰጥተው እንዲንቀሳቀሱ ጠቁመን ለዚያም መሰረታዊ ስለሆኑት የብራንድ ትርክት (brand story) እና የልኬትን አቅም መገንባት ለአንድ ተቋም ስኬታማ የዲጂታል ማርኬቲንግ ጉዞ ስለሚኖረው መሰረታዊ ሚና አንስተናል። በዚህኛው ፅሑፍ ደግሞ ለፋይናንስ ተቋማት የዲጂታል ማርኬቲንግ ምሶሶ ሊባሉ የሚችሉ ስራዎችን እናነሳለን።

1.የላቀ SEO

በኢንተርኔቱ ዓለም 70 በመቶ በላይ ጉብኝቶች የሚጀምሩት ከመረጃ ማፈላለጊያ ገፆች (search engines) ነው። 
SEO(search engine optimization )
አንድን ድረ ገፅ በመረጃ አፈላላጊዎች ዘንድ ከፊት ለፊት እንዲገኝ የሚረዳ ሲሆን ባንኮች የብድርና ቁጠባ ተቋማትም ሆነ ሌሎች የፋይናንስ ተቋማት የድረ ገጻቸውን SEO ጥሩ ደረጃ ላይ በማድረስ በፋይናንስ ዙሪያ መረጃ ለሚፈልጉ እና ጥያቄ ላላቸው የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች የእነርሱን ገጽ ቀድመው እንዲያገኙ በማድረግ ተደራሽነታቸውን እና ተቀባይነታቸውን የሚያሰፉበት ዘዴ ነው።

ኤስኢኦ (SEO) ምንድንነው? 

ጠንካራ SEO ያለው ድረ ገጽ ባለቤት ለመሆን ባንኮችና የብድር ተቋማት በመስኩ ባለሙያዎች “E-A-T” እየተባለ ስለሚጠራው የድረ ገጽ ጥራት መስፈርት በሚገባ መረዳት አለባቸው።

ታዋቂው የመረጃ ማፈላለጊያ ሥርዓት ገፅ ጎግል (GOOGLE ) በኢንተርኔት ላይ ያሉ የስህተት መረጃዎችን ለማስወገድ በሚል ይህንን “E-A-T” የተሰኘ መስፈርት በአግባቡ ይጠቀመዋል። መስፈርቱን በተወሰነ መልኩ በታትኖ ለመረዳት ያክል ‘E’ ፊደል Expertise የሚለውን ቃል ሲወክልየሙያው ባለቤትወይምበስራው የሰለጠነተብሎ ሊገለፅ ይችላል። ‘A’ ደግሞ በአንፃሩ Authority የሚለውን ሲወክልሃላፊነትወይምህጋዊ ስልጣንተብሎ በዚህ አገባብ ትርጉም ይሰጠዋል። ‘T’ ደግሞ trustworthiness የሚለውን ቃል ሲወክልተአማኒወይምእምነት ሊጣልበት የሚችልየሚል ትርጉም አለው።

ጎግል ይህን መለኪያ በተለይ ከገንዘብ ጋር ከጤና ጋር ከሰው ልጅ ሰላማዊ ኑሮ ጋር እና ደህንነት ጋር የተያያዘ መረጃ ለሚሰጡ ገጾች በተለየ ሁኔታ መመዘኛ አድርጎ ይጠቀምበታል ፡፡  ስለዚህ
የባንኮች እና የሌሎች የፋይናንስ ተቋማት ዲጂታል ገጾች በዚህ E-A-T መስፈርት መቃኘታቸው የተሻለ SEO ደረጃ ስለማግኘታቸው ዋስትና ይሰጣል።

2. ስልታዊ የመረጃ ማፈላለጊያ ስርዓት አጠቃቀም

መረጃ ማፈላለጊያዎችን ለማርኬቲንግ መጠቀም (Search engine marketing ) ስልት ለመረጃ አፈላላጊ ገጾች ክፍያን በመፈፀም ድረ ገጽን ለመረጃ አሳሽ ግለሰቦች ቀድሞ እንዲደርስ የማድረግ ስልት ነው። ከኮቪድ ወረርሺኝ በኋላ የዲጂታሉ ሚዲያ ያገኘው እጅግ ላቅ ያለ ተቀባይነት የፉክክር መጠኑን የጨመረው ሲሆን፤  በክፍያ

ድረ ገጻቸውን የተሻለ የመገኘት አቅም እንዲኖረው የሚያስደርጉ ድርጅቶች ቁጥርም ተበራክቷል። ባንኮች እና የፋይናንስ ተቋማት ለእነዚህ እንደጎግል ያሉ የመረጃ ማፈላለጊያዎች ክፍያ በመፈፀም መረጃ ጠያቂዎች በቅድሚያ እንዲያገኟቸው ማድረግ ይችላሉ። ለምሳሌ ለመረጃ አፈላላጊው ተቋም ከፍሎ ድረ ገጹን የዚህ ዕድል ተጠቃሚ ያደረገ ኢትዮጵያዊ ባንክ ለማግኘት ቢፈልግ፤ ያ ፈላጊ ግለሰብ በዚያ አፈላላጊ ገፅ ላይ ገብቶ ‘Bank’ ወይም ‘Banks in Ethiopia’ ብሎ ፍለጋውን በሚያስጀምርበት ጊዜ ከሚመጡ ውጤቶች ቀዳሚው የዚያ ባንክ ድረ ገጽ እንዲሆን ያደርጋል ማለት ነው።

3. ፈጣን ምቹ እና ለአጠቃቀም ቀላል ድረ ገጽ

ባንኮች ከላይ ያሉትን መንገዶች ከተጠቀሙ በኋላ ወደ ድረ ገጻቸው የሚመጣው ጎብኚ በቁጥር ከፍ ያለ ይሆናል። ወደገጹ የሚመጣ ደንበኛ እና እጩ ደንበኛ ድረ ገጹ ላይ በሚኖረው ቆይታ እንዲሰማው ለሚፈለገው ስሜት መጨነቅ አስፈላጊ ነው። ድረ ገጹ እነዚህን ጥያቄዎች በአግባቡ ሊመልስ ይገባል::

  •  ለአጠቃቀም ምቹ ነው?
  • በቀላሉ ሊረዱት የሚችል ነው?
  • ፈጣን ነው?
  • አማራጮቹን በፍጥነት ያሳልጣል?

እና የመሳሰሉትን ጥያቄዎች በአዎንታዊ መልኩ መመለስ መቻሉን ማረጋገጥ ይገባል። ምቾት እና ፍጥነት የባንኩ ወይም የፋይናንስ ተቋሙ ብራንድ አካል መሆኑ የግድ ነው። ተጠቃሚው ከድረ ገጹ ጋር ባለው ትስስር ምክንያት ታማኝ ደንበኞችን ማፍራት የሚቻል ሲሆን ከተወዳዳሪ ተቋማት የተሻለ የተመራጭነት አቅምንም ያዳብራል።

4. ማህበረሰቡን አሳታፊ እና አወያይ ልጥፎች

የብራንድ ትርክትን በሚቀርፁበት ጊዜ ለማህበራዊ ጉዳዮች የሚሰጡትን ዋጋ እንደአንድ መገለጫ ማሳየት ለባንኮችና ለፋይናንስ ተቋማት ወሳኝ ነው። በድረ ገጹ ላይ እና በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ማህበረሰቡ ሃሳቡን የሚገልፅበትን መንገድ ማመቻቸት እንዲሁም የውይይት መነሻ የሚሆኑ ሃሳቦችን ማጋራት ያስፈልጋል።

የፋይናንስ ተቋማቱ በማህበራዊ ችግሮች ላይ ንቁ ተሳትፎን ማድረግ እና ያንን ተሳታፊነት በዲጂታል አማራጮቻቸው ማጋራት ስሜታዊ ትስስርን ከተመልካቹ ማህበረሰብ ጋር ይፈጥራል።

ከዚያ በተጨማሪም ማህበረሰቡ ዘንድ የምክክር ሃሳቦችን እየፈጠሩ ሃሳቦች የሚንሸራሸሩበትን ሥርዓት በመዘርጋት ድረ ገጹ በተፈጥሮአዊ መንገድ ከፍተኛ SEO ደረጃ እንዲኖረው በተጓዳኝ ማገዝ ይቻላል።

5. ባለልምድና ባለተፅዕኖ የማርኬቲንግ ተቋም ጋር መስራት

በአሜሪካ ሃገር በተደረገ ጥናት በስራው የካበተ ልምድ ያላቸውና የተረጋገጠ የስኬት ታሪክ ያላቸውን የማርኬቲንግ እና የዲጂታል ማርኬቲንግ ተቋማትን ከጎን አሰልፎ ወደውድድሩ መግባት የአሸናፊነት እና የስኬታማነት ዕድልን 72 % ይጨምራል። ተቋማቱ ስራውን የማሳለጥ ልምዳቸውን እንዲሁም በዘርፉ ላይ የገነቡትን ዝና ተጠቅመው የባንኩንና የፋይናንስ ተቋሙን አቅም የሚያጎለብቱ ከመሆኑም በላይ የብራንድ አምባሳደሮችን በመቅጠር ጭምር መጠነ ሰፊ ዘመቻ ሊያደርጉ ይችላሉ።

እነዚህን ተቋማት ባንኮቹ በሚመርጡበት ጊዜ ሁለት አብየት ነጥቦችን ከግምት ሊከቱ ይገባል። የመጀመሪያው የማርኬቲንግ ተቋሙ ያለውን ልምድ፣ዕውቀት እና የውጤት ታሪክ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በዲጂታሉ ዘርፍ ያለውን አቅም እና በተለዋዋጩ የዲጂታል ዓለም ውስጥ ያለውን የፈጠራ እና አብሮ ራስን የማስኬድ ባህል ነው።

6. የቪዲዮ ፕሮዳክሽን እገዛ እና ከፍ ያለ የጥራት መጠን

የቪዲዮ ውጤቶች ባለንበት የዲጂታል ማርኬቲንግ ዘመን ያላቸው ተወዳጅነት እና ተመራጭነት ግምባር ቀደም ነው። 

ባንኮች በቪዲዮ ማስታወቂያዎች ጥራት ላይ እንደማይደራደሩ እና ቀዳሚ እንደሆኑ የቅርብ ጊዜ ልምድ ሲሆን በዲጂታል ማርኬቲንጉ ሰፊ ጥቅም ለማግኘት የሚያልም የፋይናንስ ተቋም የዲጂታል ሚዲያ አማራጮቹን እጅግ ከፍ ባለ የጥራት ደረጃ ባላቸው የላቀ ፈጠራ በታከለባቸው አዝናኝ እና ሳቢ መሆኑ የቪዲዮ ፕሮዳክሽን ስራዎች ማጀብ ይጠበቅበታል።

በዋፋ የተሰራ የባንክ ማስታወቂያ= https://youtu.be/FKFZM40ebZ0 

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top