ዲጂታል ማርኬቲንግ ለባንኮች - 1
እንደሚታወቀው ግማሽ የሚሆነው የምድራችን ህዝብ የዲጂታል ሚዲያ እና የኢንተርኔት ተጠቃሚ ነው። ይህም ማለት ገደብ የለሽ የተደራሽነት አቅም መገኛ ስፍራው የዲጂታሉ ዓለም ነው እንደማለት ነው።
የዓለማችን የኢኮኖሚ ሥርዓት በተለይ ደግሞ ከኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ በኋላ በከፍተኛ የለውጥ ሂደት እንደሚገኝ ይታወቃል። ይህ የለውጥ ሂደት ብዙ ተቋማትን ለፈተና የዳረገ እና ተቋማቱም አካሄዳቸውን መልሰው እንዲከልሱ እያስገደደ የሚገኝ ሲሆን በዘርፉ ከተፈተኑ ሴክተሮች መካከል ደግሞ የፋይናንስ ተቋማት እና የባንኮች ሴክተር ግምባር ቀደሙ ነው። ባንኮች እና የፋይናንስ ተቋማት በዲጂታሉ ዓለም ላይ በሰፊው በመቀላቀል እና የዲጂታል ማርኬቲንግ አቅማቸውን በማጠናከር ጊዜ ከፈጠረው የለውጥ መንገድ ጋር ራሳቸውን በሰፊው ማዋሃድ ይጠበቅባቸዋል። ብዙዎቹ የአገራችን ባንኮች ይህንን በተበጣጠሰም መንገድ ቢሆን ሲሞክሩት ይስተዋላል፡፡
ከደንበኞቻቸው እና ከእጩ ደንበኞቻቸው ጋር የተለየ ትስስርን ለመፍጠር ፣ በዲጂታሉ ዓለም ሚዲያዎች ፊት በተለየ አቀራረብ እና ገፅታ ለመከሰት እና የዲጂታሉን ዓለም ቱሩፋት በሰፊው ለመቋደስ የተጠና የመስኩ ተሳትፎ አስፈላጊ ነው። ነገሩ ከባድ እና ውስብስብ ቢመስልም ከጎናቸው ሁነኛ የዲጂታል ማርኬቲንግ አገልግሎት ባለሙያን በማሰለፍ እና እያንዳንዱን ሂደት በጥልቀት እና በተናጠል በተግባር በማዋል ስኬት መጎናጸፍ ይቻላል።
ባንኮች እና ሌሎች የፋይናንስ ተቋማት ከታች በዝርዝር የምንጠቅሳቸውን መሰረታዊ የዲጂታል ማርኬቲንግ ምሶሶዎች ላይ የማርኬቲንግ ዕቅዳቸውን በመገንባት ጥራት ያለው እና ተመራጭ የሆነ ብራንድ ማበልፀግ እና በሙሉ አቅማቸው ወደ ደንበኞች መድረስ ይችላሉ።
ከዚያ በፊት ግን የየትኛውም የፋይናንስ ተቋም የዲጂታል ማርኬቲንግ ዕቅድ ከግምት ሊከታቸው የሚገቡ ሁለት ዐቢይ ጉዳዮችን መመልከት ወሳኝ ነው። ይኸውም የተቋም ብራንድ ትርክት (Brand story ) እና የተቋም የስኬት ልኬት አቅም ናቸው።
የብራንድ ትርክት (Brand story) :- ማለት ለተቋም እና ለድርጅት ብራንድ የሚዘጋጅ የብራንዱን እውነታ እና ስሜት አስተሳስሮ እንዲይዝ የሚቀረፅ መገለጫ ነው። ተመልካቹ ወይም ደንበኛው ላይ የስሜት ተፅዕኖ የሚያሳርፍ ፣ መነሳሳትን በሚፈጥር መልኩ የሚቀርብ ሆኖ የብራንዱን ታሪክ ፣ የጥራት ደረጃ ፣ ዋጋ ፣ የአሰራር እና የአካሄድ ሥርዓት ፣ መገኛ ቦታ ፣ የሌሎች ሰዎች ምስክርነት እና የመሳሰሉትን አቅፎ የያዘ ትርክት ነው።
አንድ ጊዜ ይህ የባንኩ ወይም የፋይናንስ ተቋሙ የብራንድ ትርክት በሚገባ ከተቀረፀ በኋላ ወደዲጂታሉ ዓለም በሰፊው ማሰራጨት እና የተለያዩ የኢንተርኔት መንገዶች የሚዲያዎችን ባህሪይ መሰረት ባደረገ መልኩ ወደተመልካች እና ወደተከታይ ማድረስ ብራንድን የማበልፀጊያ ዘመናዊ ዘዴ ነው። ከድረ ገፅ በተጨማሪ የተለያዩ ማህበራዊ ገፆችን በትክክለኛው ጊዜ እና መንገድ ጥቅም ላይ ማዋል ከእያንዳንዱ አማራጭ የሚገኘውን ተደራሽነት እና ትኩረት አሟጥጦ ለመጠቀም ይረዳል። ሚድያዎቹን በሚመርጡበት ጊዜ ግን የሚዲያዎቹን ስልት እና የሚቀርብበትን መንገድ ማጣጣም ብቻ ሳይሆን በተመረጠው ሚዲያ ላይ የሚቀርበውን የብራንድ ትርክት ዓይነት ሚዲያውን ከሚመርጡ ተጠቃሚዎች ሥነ ባህሪይ አንፃር መቃኘትም ወሳኝ ነው። የብራንድ ሥልታዊ በሆነ መልኩ መተረክ መቻል ቀጣይነት ያለው ከደንበኞች ጋር የሚኖር ትስስርን ይለግሳል።
የቁጥራዊ ስኬት ልኬት – በእያንዳንዱ የዲጂታል ሚዲያ አማራጭ ላይ የለጠፉት የብራንድ ትርክት ምን አይነት ተቀባይነት እንዳገኘ ፣ ምን አይነት ግብረ መልስ እንደተሰጠው ፣ የትኛው ሚዲያ ላይ የተለቀቀው መልዕክት የተሻለ ተቀባይነት እንዳገኘ ፣ በየትኛው የዕድሜ ክልል ያሉ ሰዎች በተሻለ መልኩ መልዕክቱን እንደተቀበሉት… እና የመሳሰሉትን መረጃዎች መሰብሰብ እና መተርጎም ፤ በመቀጠልም መተንተን ሌላኛው የፋይናንስ ተቋማት በዲጂታል ማርኬቲንግ ላይ ሊጥሉት ላሰቡት መሰረት አይነተኛ የማዕዘን ድንጋይ ነው።
ለእነዚህና ሌሎች የዲጂታል ማርኬቲንግ ፍላጎትዎ ዋፋ ማርኬቲንና ፕሮሞሽን አለሁ ይላል፡፡ ዋፋ ማርኬቲንግና ፕሮሞሽን የተቀናጀ የማርኬቲንግና የኮሙኒኬሽን አገልግሎትን የሚያገኙበት ተቋም ነው፡፡
(ክፍል ሁለት በቀጣይ ይቀጥላል)