ልዩ ፈጠራ የታከለባቸው ማስታወቂያዎች

ልዩ ፈጠራ የታከለባቸው ማስታወቂያዎች

ስለማስታወቂያዎች ትንሽ እንጨዋወት? በዓለማችን ላይ ተቋማት በየአመቱ በበርካታ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ማስታወቂያዎችን ይሰራሉ ያሰራሉ። ለእነዚህ ማስታወቂያዎች ደግሞ በበርካታ ቢልዮን ረብጣ ዶላሮች ፈሰስ እንደሚደረጉ የአደባባይ ሚስጥር ነው። የማስታወቂያዎቹ ቁጥር የመብዛቱን ያክል በሀሳብ ድግግሞሽ በደረቀ የፈጠራ አቅም እና በአሰልቺነት ምክንያት የወጣባቸውን ወይም የተለፋባቸውን ያክል ዒላማቸውን ሳይመቱ በኪሳራ የሚያበቁ ማስታወቂያዎች ቁጥር ቀላል አይደለም። በዛው ልክ ደግሞ የተለየ የፈጠራ አቅምን በመጠቀም ቀላልነትን በተላበሰ መልኩ ተሰርተው ከታለመላቸው ዕቅድ በላይ ዒላማቸውን ያሳኩ ማስታወቂያዎችም በርካቶች ናቸው። እነዚህ ማስታወቂያዎች አንድ ማስታወቂያ ከተለመደው የአሰራር መንገድ ወጣ ብሎ መዘጋጀት ከቻለ ያለብዙ ልፋት ስኬታማ እንደሚሆን ማሳያ ናቸው። ለዛሬ ከእነዚህ ማስታወቂያዎች መካከል በቢልቦርድ እና በፖስተር የማስታወቂያ መንገድ የተሰሩትን እንመልከት።

 

የፓስታ ማስታወቂያ ነው። ርችት ይመስላል አይደል? ለደንበኞቻቸው መልካም አዲስ አመት የተመኙት ምርታቸውን በተለየ አንግል ፎቶ በማንሳት ርችት በማስመሰል ነበር።

ፓስታ -> ርችት_______ርችት-> ፓስታ

ታዋቂው ድምፃዊና ተዋናይ ጀስቲን ቲምበርሌክ ነው የሰራላቸው። የማክዶናልድ ማስታወቂያ! ሴት አይደለችም አጠገቡ ያለው በርገር ነው። እና ለመሳም የተዘጋጀ ቢመስልም አይደለም በርገር ሊገምጥ እንጂ… am lovin it ከሚለው motto ጋር የሚሄድ አሪፍ የቦርድ ማስታወቂያ ሰርተዋል።

 

 

 

 

ሄይንዝ የሚባል Hot ketchup ቦርድ ነው። Hot መሆኑን ለመግለፅ አስር ጊዜ Hot Hot ብሎ ከመፃፍ ቺፕሱ ካቻፑን ሲነካው መቃጠሉን ማሳየት ምን ያህል “HOT” እንደሆነ በግነት ዘዬ ለማስረዳት ይመቻል። እውነትም HOT !

የዋይልድ ላይፍ ተቋም የሰራው ማስታወቂያ ነው። Horrifying እና More Horrifying በሚል ንፅፅር ሁለት ፎቶዎች አስቀምጧል። የመጀመሪያው የሻርክን መኖር ለሰው ልጆች አደገኝነት የሚገልፅ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የሻርክ ከምድረ ገፅ መጥፋት ለሰው ልጅ የበለጠ አደጋ አለው የሚል ነው። በተፈጥሮ ሳይንስ ውስጥ Food chain የሚባል የፍጥረት ስርዓት አለ ይህ የተያያዘ ተፈጥሮአዊ ስርዓት አንዱ ጋር ሲቋረጥ አደጋው ከባድ እንደሆነ ባለሙያዎቹ አበክረው ይናገራሉ። ስለዚህ…. ጥንቅቄ ለዱር እንስሳት!

ከስኳር ነፃ ሎሊፖፕን ለማስተዋወቅ የተጠቀሙበት መንገድ ነው።ቁጫጮቹ ያለፉት ስኳር ስለሌለው ነውነው መልእክቱ ቀላል ግን ድንቅ ፈጠራ!

የጫማ መደርደሪያ (ሹዝ ራክ) ሰሪ ተቋም ማስታወቂያ ነው። Need space? ይላል መሪ ቃሉ! የወንድ All Star ጫማን በሴት Heel ጫማ ስር የተቀመጠው እንግዲህ በቦታ እጥረት የመጣ መሆኑ ነው። ስለዚህ አሪፍ ቀለል ብሎ ሰፋ ያለ ሹዝ ራክ እኛ ጋር አለ እያሉ ነው።

የሄልሜት ማስታወቂያ ነው። የሳይክል ሄልሜት! ሰውዬው አደጋ ደርሶበት ያልተጎዳው የሰውነቱ ክፍል የለም። ከጭንቅላቱ በስተቀር! ምን አይነት ሄልሜት ቢጠቀም ነው? ያለጥርጥር የሳይክል ወዳጆች በማስታወቂያው ትኩረታቸው ይሳባል።

 

 

 

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top