company profile

ተቋምዎ ለምን ደረጃውን የጠበቀ “ካምፓኒ ፕሮፋይል” ያስፈልገዋል?

ካምፓኒ ፕሮፋይል ድርጅትዎ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ራሱን የሚገልፅበት መንገድ ነው። ድርጅቱ የተመሰረተበት ዓላማ፣ ራዕይና ግቡ፣ የተመሰረተበት መንገድ፣ የአገልግሎት ዘመኑና ስኬቱ፣ የምርቱ ወይም የአገልግሎት አሰጣጡ ጥራት፣ ያገኛቸው ሽልማቶችና ምስክርነቶች፣ ድርጅቱን እየመሩት ያሉ ባለሙያዎች… እና የመሳሰሉትን በማካተት ደንበኛ እንዲሆን ትኩረት የተሰጠው አካል ስለድርጅቱ በቂ ቅድመ መረጃ እንዲያገኝ እና አብሮ መሥራቱ የሚያስገኝለትን ቱሩፋት እንዲያስብ የሚያስችል መስህብ ነው።

 ተቋማት አብረዋቸው እንዲሰሩ የሚያስቧቸውንና የሚጋብዟቸውን ድርጅቶችና ተቋማት ላይ ጥናት ሲያደርጉ በቅድሚያ የሚመለከቱት የካምፓኒውን ፕሮፋይል በመሆኑ በጥራት፣ በጥንቃቄና በትኩረት ሊዘጋጅ የሚገባው ነው።

ደረጃውን የጠበቀ ‘ካምፓኒ ፕሮፋይል’ ማዘጋጀት ለአንድ ድርጅት ያለው ጠቀሜታ ምንድ ነው?

1. ‘ካምፓኒ ፕሮፋይል’ እንደዋነኛ የማርኬቲንግ መሳሪያ

ለተቋምዎ ደረጃውን የጠበቀ ፕሮፋይል ካዘጋጁለት በገበያው ላይ ራስዎን በሚገባ የሚገልፁበትን መድረክ ፈጠሩ ማለት ነው። ጥራት ያለው ፕሮፋይል ካዘጋጁ በኋላ ቴክኖሎጂው ባፈራቸው አማራጮች ከህትመት እስከ ዲጂታል ሚዲያ በመጠቀም ተደራሽነቱን በማስፋት የድርጅቱን ማንነት፣ ምንነትና ምርት ወይም አገልግሎት ለሚፈለገው ዒላማ(Target Group) ስልታዊ በሆነ ሁኔታ ማድረስ ይችላሉ። በተቋሙ ዌብሳይት የፊት ገፅ ላይ፣ በማህበራዊ ትስስር ገፆች(Facebook, LinkedIn , twitter) እንዲሁም የህትመት ውጤቶችን በመጠቀም የማርኬቲንግ ስራዎን እንዲደግፉ ያስችላል። ከእርስዎ ድርጅትጋር ለመስራት ፍላጎት ላደረባቸው ተቋማትም መረጃዎችን በአንድ ቦታ እንዲያገኙ ያስችላቸዋል፡፡

2. ጎልተው የሚታዩበትን ዕድል ይፈጥራል

የእርስዎ ድርጅት የተሟላና ደረጃውን የጠበቀ ፕሮፋይል ካለው ከሌሎች ተወዳዳሪዎችዎ የተሻለ ተመራጭነት ይኖረዋል። የድርጅትዎ ራዕይና ተልዕኮ በግልፅ ከተቀመጠ፣ ስኬትና ሽልማቶችዎ በመረጃ ተደግፎ ከተመሰከረ፣ የአሰራር መንገድዎ ጥራትና ታማኝነቱ ከቀደሙት ስራዎች እየተጣቀሰ በሚገባ ከተገለፀ ተፎካካሪዎን አንድ እርምጃ ቀድመው ተገኙ ማለት ነው፡፡

3. የተቋምን ‘ብራንድ’ ይገነባል

የአንድ ተቋም ብራንድ(መለያ) በቀላሉ አይገነባም። የብራንድ ግንባታ ሂደት የዓላማና ግብ፣ የአሰራር ሥርዓት፣ የአገልግሎት ወይም የምርት ዓይነትና ጥራት፣ የታሪክ ፣ የቀለም ምርጫ፣ የማስታወቂያና የመሰል በርካታ ግብአቶች ድምር ውጤት ነው ። በዚህ የብራንድ ግንባታ ሂደት የማስተዋወቂያው ዋነኛ መሳሪያ ደግሞ ‘የካምፓኒ ፕሮፋይል ‘ ነው። የዳበረ እሴት የፈጠረ ብራንድ በካምፓኒ ፕሮፋይል ሲገለጽ ነባር ደንበኞችን አብረው እንዲቀጥሉ ከማስቻሉም በላይ አዳዲስ ደንበኞችም አብሮ ለመሥራት ፍላጎት እንዲያድርባቸው ያነሳሳል፡፡ ታላሚ ደንበኞች (Prospects) በእርስዎ ድርጅት ላይ የሚያሳድሩት አመኔታ ለድርጅትዎ ዕድገት ወሳኝ እንደመሆኑ ያንን አመኔታ ለመፍጠር የሚያዘጋጁት ደረጃውን የጠበቀ ‘ካምፓኒ ፕሮፋይል’ እገዛው ከፍተኛ ይሆናል።

4. ለተቋምዎ እንደመስኮት ያገለግላል

ፈጠራ የታከለበትና ከተለመደው ለየት ያለ ‘የካምፓኒ ፕሮፋይል’ ለድርጅትዎ ልክ እንደ አንድ የመደብር መስኮት ያለ ግልጋሎት ይሰጣል። ምርት ወይም አገልግሎትዎን በፈላጊዎች ልቦና ከተፎካካሪ ተቋማት በተሻለና በቀላሉ እንዲታወስ ማድረግ የሚችል ፕሮፋይል ካዘጋጁ በገበያው ስፍራ የፊት ለፊቱን ቦታ ተቆናጠጡ እንደማለት ነው።

5. ተመራጭ ያደርጋል

‘ካምፓኒ ፕሮፋይል’ እንደአንድ ግለሰብ የስራ ዝግጅት “CV” ያለ ሚናም አለው። በእርስዎ አይነት የስራ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ አምራቾች ወይም አገልግሎት ሰጪዎችን ለማሰስ የወጣ አንድ ተቋም በቅድሚያ የሚመለከተው አገልግሎቱን ለመስጠት በገበያው ላይ ያሉ ድርጅቶችን ‘ካምፓኒ ፕሮፋይል’ በመሆኑ ደረጃውን የጠበቀ (Professional ) ፕሮፋይል ማዘጋጀት ማለት ለስራው የተሻለ ቁመና ላይ እንደሚገኙ የማሳያ ጥበብ ነው።

ያዘጋጁት ፕሮፋይል በምርቱ ወይም በአገልግሎት ፈላጊው ዘንድ ተአማኒነትን ከፈጠረና ለስራው ብቁ የሆነ ቁመና ላይ የሚገኘው ድርጅት የእርስዎ ድርጅት ስለመሆኑ ሙሉ መተማመንን ካሳደረ ቀጣዩ እርምጃ የሚሆነው ወደተቋምዎ የሽያጭ እና የማርኬቲንግ ክፍል ስልክ መደወል ወይም መልዕክት መላክ ስለመሆኑ እርግጠኛ መሆን ይችላሉ።

ካምፓኒ ፕሮፋይል ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ በመሆኑም የዝግጅት ስራው በባለሙያ የሚከናወንና ጥልቅ እይታን የሚፈልግ ነው፤ካምፓኒ ፕሮፋይል በጽሁፍም ሆነ በቪዲዮ ለማዘጋጀት በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ ያላቸውን ድርጅቶች ማማከር ወይም ማሳተፍ የሚያስፈልገውም ለዚህ ነው፡፡ ዋፋ ማርኬቲንግና ፕሮሞሽን የሚፈለገውም እዚህ ላይ ነው፤ የካበተ ልምድና ብቁ ባለሙያዎችን ይዞ ለበርካታ ድርጅቶች ካምፓኒ ፕሮፋይልና ሌሎችም ፕሮዳክሽኖችን በመሥራት የማርኬቲንግ ግባቸውን እንዲያሳኩ ያገዘውና በዘርፉ መልካም ስም የገነባው ዋፋ ማርኬቲንግና ፕሮሞሽን በዚህ ረገድ ሁሌም ሊገለግልዎ ዝግጁ ነው፡፡

 

 

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top