5 የጊዜው የዲጂታል ማርኬቲንግ ፈተናዎች

ግዙፉ የፕሮፌሽናል አገልግሎት ተቋም ዴሎይት(Deloitte) በቅርቡ ያወጣው መረጃ እንደሚጠቁመው የኮሮና ቫይረስ በዓለም ዙሪያ መከሰት የማርኬቲንግ ስራን አስፈላጊነት 72 በመቶ ጨምሮታል። በተለይ ደግሞ የዲጂታል ማርኬቲንግ ሚና ከየትኛውም ጊዜ በላይ አስፈላጊ ወደመሆን የተቀየረበት እና ተፅዕኖው የጎላበት እንደነበርም መረጃው ያትታል። ይህ የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ የተንሰራፋበት እና አብዛኛው ማህበረሰብ በቤት ውስጥ የመቆየት አስገዳጅ ደንብ የተጣለበት ወቅት በዲጂታል ማርኬቲንጉ ዘርፍም የደንበኞች ስነባህሪይ በተወሰነ መልኩ የተለወጠበት እንደመሆኑ አዲስ የአኗኗር ዘይቤን ለመላመድ በሚያደርገው ጥረት ውስጥ አብዛኛውን የግብይት ሥርዓት በኦንላይን ለማድረግ የተገደደበት ሁኔታ ተፈጥሯል።

 

ይህ የደንበኞች የባህሪይ መለወጥ የዲጂታል ማርኬቲንግ ባለሙያዎችንም ሚናቸውን እና አሰራራቸውን እንዲከልሱ አስገድዷል። ይህም የደንበኞቻቸውን ሰፊ ፍላጎት ለማርካት እና በውድድሩ ላይ ተሽሎ ለመገኘት አስፈላጊነቱ የጎላ በመሆኑ ነው። ዘመኑ ካፈራቸው ቴክኖሎጂዎች ጋር ራስን አስማምቶ የመጓዝ ሂደቱም የዚህ እንቅስቃሴ አካል ተደርጎ ይወሰዳል። በዚህ እና በሌሎች ፈተናዎች ምክንያትም የዲጂታል ማርኬቲንግ ዘርፉ በሽግግር ወቅት ላይ መገኘቱ የአደባባይ ምስጢር ነው ከነዚህ ፈተናዎች መካከል የሚከተሉት ዋነኞቹ ናቸው።

1. ደንበኛን ያማከለ ገበያ

ደንበኛን ማዕከሉ ያደረገ የገበያ ስርዓትን ከራስ የአሰራር መንገድ ጋር ማላመድ ቀላል ኃላፊነት አይደለም። በተለይ የደንበኛ ፍላጎት እና ጠባቂነት በየጊዜው እየተለወጠ መሄዱ ደግሞ ስራውን የበለጠ ያከብደዋል። ሆኖም ይህንን የደንበኛን ያማከለ የማርኬቲንግ ሥርዓት ሥልትን መጠቀም ለወቅቱ ስኬታማነት ቁልፍ እንደሆነ ጥናቶች ያስረዳሉ። በጥናቶቹ መሰረትም፡-

·        66% ተጠቃሚዎች (ደንበኞች) የአንዱ ተቋም አገልግሎት እና አቀራረብ ለቀጣዩ ድርጅት በሚኖራቸው ምልከታ ላይ ተፅዕኖ ያሳርፋል።

 

·        52% ተጠቃሚዎች (ደንበኞች) የሚቀርቡላቸው አማራጮች በቀጥታ ለእነርሱ በግል ወይም በተቋም ደረጃ የተቀረፀ እንዲሆን ይሻሉ።

·   66% ተጠቃሚዎች (ደንበኞች) አገልግሎቱን የሚያቀርቡላቸው ድርጅቶች የእነሱን የተለየ ፍላጎት እንዲረዱላቸው ይፈልጋሉ። ሆኖም እነዚህ 66 በመቶ ደንበኞች በተቋማት ከቁጥር ያለፈ ዋጋ እንደሌላቸው ያስባሉ።

·  48% በመቶ የሚሆኑት ደንበኞች(ተጠቃሚዎች) ብቻ ምርት እና አገልግሎት በሚሰጧቸው ተቋማት ላይ ሙሉ እምነት እንዳላቸው ይናገራሉ።

       

ከጥናቶቹ እንደምንረዳው የዲጂታል ማርኬቲንግ ዓለምን የተቀላቀሉ ብቻ ሳይሆን ያልተቀላቀሉ ተቋማትም ወደዚህ ሰፊ እና አዲስ ዓለም ሲቀላቀሉ የደንበኞችን ፍላጎት ለመረዳት ጥልቅ ጥናት ሊያደርጉ እንደሚገባ ነው።

2. አሳታፊ ልጥፎችን መፍጠር እና ማጋራት

ተመልካችን አሳታፊ ልጥፎችን መፍጠር እና ማጋራት ሌላኛው የወቅቱ የዲጂታል ማርኬቲንግ ፈተና ነው። የተመልካቹ ፍላጎት በሚገርም ፍጥነት እየተቀየረ በመሆኑ እና ቀልቡን የሚስቡ ልጥፎች ከየአቅጣጫው የሚጎርፉለት በመሆኑ፤ ያንን ትኩረት ወደራስ ለመሳብ እና ለማቆየት በየጊዜው ፈጠራ የታከለባቸው ማራኪና አስተማሪ ልጥፎች (Content) በማጋራት ተመልካቹ ከማየት እና ከማንበብ ባለፈ ራሱን በተለያዩ መንገዶች ተሳታፊ የሚያደርግበትን መንገድ መፍጠር ግዴታ ነው። 

3. ከግላዊነት እና ከመረጃ ጥበቃ ደንቦች ጋር መግባባት

ጥናቶች እንደሚያሳዩት ተቋማት የግል መረጃዎቻቸውን እንዴት እንደሚጠቀሙ ግንዛቤ ያላቸው ተጠቃሚና ደንበኞች 27% በመቶ ብቻ ናቸው። ከጠቅላላ ተጠቃሚዎች መካከልም 86 % የሚሆኑት ደንበኞች በመረጃ አጠቃቀማቸው ዙሪያ ተቋማት ግልፅ እንዲሆኑላቸው ይፈልጋሉ።

 

የዲጂታል ማርኬቲንግ መስክ ላይ ያሉ ተቋማትም ሆኑ በዲጂታል ማርኬቲንጉ ላይ ተሳትፎ ለማድረግ የሚያስቡ ድርጅቶች በለውጥ ላይ የሚገኘውን የግላዊነት ደንብ መረዳት እና ድረ ገጾቻቸው ላይ የሚገኙት የግል መረጃዎች በሌላ ሶስተኛ ወገን ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ደህንነቱ የተጠበቀ ድረ ገፅ ሊያዘጋጁ ይገባል። ዘመኑ አገልግሎትን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማሳደግ ዲጂታል ማርኬቲንግን ምርጫው ያደረገ በመሆኑ እና ድረ ገጾችም ዓለም አቀፋዊ ተደራሽነታቸው እየጨመረ ያለበት ጊዜ በመሆኑ በየትኛውም የዓለም ክፍል የሚገኝ ተገልጋይ ዒላማ ሊደረግ ይችላል ፤ ስለዚህ ዒላማ ያደረግናቸው ግለሰቦች የሚገኙበትን ሃገር ወይም ስፍራ ላይ ያለውን የግላዊነት ደንብ (Privacy Regulations ) ማጤን አስፈላጊ ነው። 

4. ለሞባይል ስልክ የተመቸ አቀራረብ

 ደንበኞች ለመገበያየት እና የተለያዩ አገልግሎቶችን ለማግኘት ድረ ገጾችን ሲያስቡ በሞባይል ስልኮቻቸው የሚጠቀሙበት መጠን ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍ ብሏል። ከኦንላይን ግብይቶች መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆነው የሚፈፀመው በሞባይል አማካኝነት ነው። በመሆኑም ተቋማት የሚያዘጋጁት ድረ ገፅ ለሞባይል አጠቃቀም ምቹ መሆኑን ማረጋገጥ ተቀዳሚ ግዴታቸው ሆኗል። አንድ ጥናት እንዳሳየው ኮቪድ ደንበኞች በሞባይል ግብይት ላይ ያላቸውን አቋም እስከወዲያኛው የቀየረው ሲሆን በስልኮቻቸው ላይ የሚያጠፉት ጊዜም ከወትሮው በ 25 % አሻቅቧል።

5. ሁለገብ የማርኬቲንግ ሥልት

የዲጂታል ማርኬቲንጉ ዓለም ሁሉንም የሚዲያ አማራጮች ሊጠቀምበት ይገባል። ኢሜል ማርኬቲንግ እስከ ማህበራዊ ትስስር ድረ ገፅ(social media) ፣ ከግል ድረ ገፅ ጀምሮ በክፍያ በሌላ ገፅ ላይ እስከማስተዋወቅ ድረስ ፣ ከአፕሊኬሽኖች ማስታወቂያ እስከ አጭር የፅሁፍ መልዕክት(SMS)  ድረስ ሁሉንም አማራጮች ከመጠቀም መቦዘን ከወቅቱ ውድድር ያስወጣል። ከ74% በላይ ተጠቃሚዎች አንድን አገልግሎት ወይም ምርት አይተው ለመጠቀም እስከመወሰን ባለው ሂደት ውስጥ ከአንድ በላይ የሚድያ አማራጮችን ጥቅም ላይ ያውላሉ።

 

ስኬታማ እና ወቅታዊ የማርኬቲንግ ሥልቶችን ለመጠቀም የተሟላ አቅም ያለው እና ሁነኛ የዲጂታል ማርኬቲንግ ቡድን ያስፈልግዎታል። ጋርትነር የተባለው ታዋቂ ተቋም በቅርቡ ባጠናው ጥናት 35 በመቶ የሚሆኑ የማርኬቲንግ ሰዎች ዋነኛ ተግዳሮት ብለው የጠቀሱት ሁነኛ እና የተደራጀ የዲጂታል ማርኬቲንግ ቡድን አለማግኘትን ነው። 

ጥቂት ስለዲጂታል ማርኬቲንግ ቡድን

በ21 መቶ ክፍለ ዘመን የማርሉቲንግ ሳይንስ ግብይት የዲጂታሉን ዓለም አውድ በአግባቡ መተቀም ላይ ያኩራል፡፡ ይህ ታዲያ በሰለጠነ የዲጂታል የባለሙያዎች ቡድን የሚሰራ ነው፡፡ የዲጂታል ማርኬቲንግ ቡድን ለማዋቀር በሚያስቡበት ጊዜ በቅድሚያ ስራው የሚፈልገውን ችሎታ እና ቡድናዊ መናበብ ሊያውቁ ያስፈልጋል። ይህን ካጠናቀቁ በኋላ ምን አይነት አቅም ያላቸውን ሰዎች በቡድናቸው ውስጥ ማካተት እንደሚገባ ማወቅ እና ቡድኑን ማዋቀር አይከብድም።

 

ተቋማችን ዋፋ ማርኬቲንግ እና ፕሮሞሽን ለድርጅትዎ በዲጂታል ማርኬቲንጉ ዘርፍ ከማማከር አንስቶ ባለን የተደራጀ የዲጂታል ማርኬቲንግ ቡድን አማካኝነት የእርስዎን ተቋም ወደዲጂታል ማርኬቲንጉ ዓለም በሰፊው ለማስገባት ዝግጁ ነው።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top