ኢሜይል ማርኬቲንግ ምንድነው?

ኢሜይል ማርኬቲንግ ምንድነው?

ኢሜይል መደበኛ የግንኙነት መንገድ እንደሆነ ይታወቃል። አንድን ግለሰብ ወይም አካል ለስራ ወይም ለተለያየ የቢዝነስ እና የአገልግሎት ጉዳይ ማናገር ሲፈልጉ ኢሜይል ተመራጩ መንገድ መሆኑ የሚታወቅ ነው። ኢሜይል ለተቋምዎ የዘመናዊነትን የፕሮፌሽናልነትንና የምሉዕነትን ገፅታ ያላብሳል።

      የዲጂታል ማርኬቲንግ ባለሙያዎች ምርት ወይም አገልግሎታቸውን ለተጠቃሚዎቻቸው ከሚያስተዋውቁባቸው ስልቶች አንዱ የኢሜይል ማርኬቲንግ ስልት ነው። ተቋምዎ አዲስ ምርት ወይም አገልግሎት ስለመጀመሩ ለደንበኞችዎ ከሚያሳውቁባቸው መንገዶች አንዱ በኢሜይል የሚደርስ መልዕክት ነው። በተጨማሪም የዋጋ ማሻሻያ መረጃዎች ለእይታ የሚቀርቡ ሁነቶችን ለማስተዋወቅ ኢሜይል ተመራጭ እና ወጪ የማይጠይቅ ዘዴ እንደሆነ መጥቀስ ይቻላል።           

የኢሜይል ማርኬቲንግ ለውጤታማነት ቅርብ ነው። ይህም የሆነበት ምክንያት ተጠቃሚዎች እና ደንበኞች ወደተቋምዎ ድረ ገፅ በመጎብኘት ለምርቱ ወይም አገልግሎቱ ስላላቸው ፍላጎት ፍንጭ ስላሳዩ ነው። ይህ በመሆኑ ኢሜይል ማርኬቲንግ በማርኬቲንግ የአዲስ ደንበኝነት ሂደት ደረጃ ውስጥ ሁለተኛ  ላይ ከሚገኘው የቅድመ ውሳኔ ደረጃ (Consideration stage) ወደ ውሳኔ ደረጃ ለመቀየር በሰፊው ጥቅም ላይ ይውላል። በተጨማሪም በኢሜይል ማርኬቲንግ ስልት በመጠቀም ምርትና አገልግሎትን መሸጥ ስለብራንድ ግንዛቤን ማስጨበጥ እንዲሁም ደንበኞችን ታማኝ ሆነው እንዲቆዩ ማድረግ ይቻላል። 

በማርኬቲንግ ውስጥ ሶስት አይነት የኢሜይል መልዕክቶች ያሉ ሲሆን መረጃ ሰጪ መልዕክቶች ማስተዋወቂያ መልዕክቶች እና ቀስቃሽ መልዕክቶች ይባላሉ።

መረጃ ሰጪ መልዕክቶች (Informational emails)

እነዚህ የኢሜይል መልዕክቶች ለደንበኞች ስለአዳዲስ ምርቶች ወይም አገልግሎቶች መረጃ የሚሰጡባቸው መልዕክቶች ናቸው። መረጃዎቹም በዜና መልክ ወይም በመግለጫ መልክ ሊቀርቡ ይችላሉ።

ማስተዋወቂያ መልዕክቶች(Promotional emails)

አዳዲስ ምርቶች ወይም አገልግሎቶች የዋጋ ቅናሾች እና ልዩ የዋጋ ዕድሎች ተጨማሪ ጥቅማጥቅሞችንና የመሳሰሉትን ያካተቱ መልዕክቶችን በዘመቻ መልክ የሚያደርሱበት የኢሜይል መልዕክት አይነት ነው።

ቀስቃሽ መልዕክቶች(Re-engagement emails)

ከዚህ ቀደም ከተቋምዎ ጋር አብሮ የመስራት ምርት እና አገልግሎትን የመግዛት እና የመጠቀም ልምድ ያላቸው ሆነው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን የጠፉ ደንበኞችን ደንበኝነታቸውን እንዲያድሱ የሚቀሰቅሱበት የኢሜይል መልዕክት አይነት ነው።

ጥሩ የማርኬቲንግ የኢሜይል መልዕክቶችን ለመፍጠር ምን ያስፈልጋል?

ለኢሜይል ማርኬቲንግ ቀዳሚው ወሳኝ ጉዳይ ቀስቃሽ መልዕክት ማዘጋጀት (Copy writing) ነው። አሳማኝ ይዘት ያለው መልዕክት ደንበኛን ለተጨማሪ የምርት ወይም የአገልግሎት ተጠቃሚነት እና ግዢ ያነሳሳል። ሌላኛው ጉዳይ ደግሞ ጥሩ የኢሜይል ዲዛይን ነው። ለኢሜይል ማርኬቲንግ ስራ ምቹ የሆነ ዲዛይን ማዘጋጀት ቀላል ነው። ኢንተርኔት ላይ በክፍያ እና ያለክፍያ የሚገኙ በርካታ የኢሜይል ቴምፕሌቶችን ማግኘት ይቻላል። በተጨማሪም እንደነ Canva ባሉ የዲዛይን መተግበሪያዎች በሚፈልጉት መልኩ ማዘጋጀትም ሌላኛው መንገድ ነው።

 

ኤሜይል ማርኬቲንግን እንደአንድ የማርኬቲንግ መሳሪያ ለመጠቀም  የኢሜይል አገልግሎት ሰጪ ተቋም ያስፈልግዎታል ። ለዚህ ደግሞ ዋፋ ማርኬቲንግና ፕሮሞሽን አለልዎ!

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top