digital marketing for real estate

ዲጂታል ማርኬቲንግ ለሪል ስቴቶች

እንደሌሎች የስራ መስኮች ሁሉ የሪል ስቴት ኢንዱስትሪውም የዲጂታል ማርኬቲንግን እገዛ እጅጉን የሚፈልግበት ዘመን ላይ ደርሰናል። በሀገራችን የሪል ስቴት ልማት ላይ ያለው ጠንካራ ፉክክር ተቋማትን ከተፎካካሪዎቻቸው የተሻለ የማርኬቲንግ ተሳትፎ እንዲያደርጉ እና ዘመኑ ከሚፈጥራቸው አማራጮች ጋር አብረው እንዲጓዙ ያስገድዳል።።

ዲጂታል ማርኬቲንግ የራሱን ሰፊ ልፋት እና ጊዜ የሚጠይቅ ቢሆንምbየመስኩ እገዛ ሳይታከልበት ለስኬት የመብቃት ጉዳይ ግን በድህረ ዘመናዊነት ዓለም የማይታሰብ ሆኗል። የሪል ስቴት ኢንዱስትሪው እጅግ በበለፀገባቸው ሀገራት የስኬታማነት መጠናቸው ከፍ ያሉ ተቋማት በዲጂታሉ ዓለም የተሻለ እና የሰለጠነ ተሳትፎን የሚያደርጉት ናቸው።
በዲጂታል ማርኬቲንጉ ምንም ተሳትፎ የሌላቸው ወይም አናሳ ተሳትፎን የሚያደርጉ የሪል ስቴት ኩባንያዎች በተፎካካሪዎቻቸው ኋላ የሚቀሩበት
ዕድል የሰፋ ነው። 
ስራው ብዙ ስልት እና መጠነ ሰፊ የተግባር እንቅስቃሴ የሚጠይቅ ቢሆንም አንድ የሪል ስቴት ተቋም በዲጂታሉ ዓለም ላይ ያለውን ህልውና ለማረጋገጥ ከዚህ በታች የሚገኙትን ትግበራዎች በአግባቡ ማከናወን ይጠበቅበታል።

ትኩረት ለድረ -ገጽ

የሪል ስቴት ኩባንያዎች የራሱ ድረ ገጽ ከሌለው በፍጥነት የመጀመሪያ እርምጃ ሊያደርጉት የሚገባው ደረጃውን የጠበቀ ድረ ገጽ እንዲኖረው ማድረግ ነው። ድረ ገጹ ተቋሙን እንደመወከሉ መጠን የጥራት ደረጃው የላቀ እና ፕሮፌሽናል ገጽ መሆኑ የሚጠበቅ ይሆናል። ቤት የመግዛት ፍላጎት ያደረበት ሰው በቅድሚያ ሊያደርግ የሚችለው ነገር ቤት አቅርቦት ላይ የተሰማሩ ኩባንያዎችን ከኢንተርኔት ላይ በማፈላለግ ስለሚሰጡት አገልግሎት ፣ ስለተዘጋጁ ቤቶች እና ዋጋ የመሳሰሉ መረጃዎችን ማሰስ ነው ። በዚህ ሂደትም ግለሰቡ ከሚያገኛቸው መረጃዎች በተጨማሪ በተቋሙ ላይም የአመኔታ ስሜት ይፈጠርለታል። ስለሆነም የተቋምዎ መረጃዎች በአግባቡ ተሰድረው እንዲቀርቡ የሚያስችል ድረ ገጽ መዘጋጀቱን ማረጋገጥ ግዴታ ነው።

ሆኖም ግን ጥሩ እና ለአጠቃም ምቹ የሆነ እና በጥሩ ጥሩ መረጃዎች የታጨቀ ድረ ገጽ ባለቤት መሆን ብቻውን በቂ አይደለም። ቤት ገዢዎችና ሌሎች ዒላማዎች በቀላሉ ሊያገኙት የሚችሉትን ድረ ገጽ መፍጠር ያስፈልጋል። ለዚህም ይረዳ ዘንድ ኩባንያዎ የድረ ገጹን SEO የማበልፀግ ስራን ሊሰራ ይገባል። ይህ ከሆነ ገጹ ባለው የተሻለ SEO ምክንያት ከፊት መገኘት የሚችል ሲሆን ካልሆነ ግን በሌሎች ተፎካካሪ ተቋማት ገጾች የመሸፈን እጣ ይገጥመዋል

SEO ምንድነው?

የማህበራዊ ትስስር ገጾች (Social Media Accounts )

እንደድረ ገጹ ሁሉ የማህበራዊ ትስስር ገጾችም ፍጹም ችላ ሊባሉ የማይገባቸው የዲጂታል ማርኬቲንግ መሳሪያዎች ናቸው። በአግባቡ ጥቅም ላይ ከዋሉ በዋጋ ሊተመን የማይችል ውጤት አላቸው። ስለሆነም የሪል ስቴት ኩባንያዎ በተለይ ዋነኛ በሆኑ እና ዓለም አቀፍ ተጠቃሚያቸው ከፍተኛ የሆኑ እንደነ ፌስቡክ ፣ ትዊተር ፣ ኢንስታግራም እና ሊንክዲን እንዲሁም የዩቲዩብ ገፅ በመክፈት እና ተደራሽነትን ማስፋት እና የመረጃ ጥምን መቁረጥ ይጠበቅበታል።

ማህበራዊ ሚዲያዎችን በተመለከተ ትኩረት ሊደረግበት የሚገባው ጉዳይ ገጾቹን ከመክፈት እና የአካውንት ባለቤት ከመሆን ባለፈ የተደራሽነቱ ጉዳይ ነው። በተለይ በጀማሪነት ደረጃ ላይ የሚገኝ ድረ ገጽ ያላቸው ተቋማት የማህበራዊ ሚዲያ ማስተዋወቂያ (Social media Ads) ክፍያ በመፈፀም የገጻቸውን ተደራሽነት ሊያሻሽሉ ይገባል።

የተሟሉ ልጥፎች (Complete Contents)

 ቤት የመግዛት ውሳኔ ትልቅ ውሳኔ ነው። ለግዢ የሚመጣው ግለሰብ (አካል) የመጀመሪያ ግዢውም ሆነ ከዚህ በፊት ልምድ ያለው በውስጡ ብዙ ጥያቄዎችንና ስጋቶችን ይዞ እንደሚመጣ አይጠረጠርም። ስለዚህ ወደድረ ገጽዎም ሆነ ወደ ማህበራዊ ገጾችዎ የሚመጣ ሰው ለእነዚህ የቤት ግዢ ጥያቄዎቹ አጥጋቢ መልስ የሚሰጡ ልጥፎች (Contents) ሊዘጋጁለት ይገባል።

አካላዊ ያልሆኑ ጉብኝቶች ( Virtual tours)

የቤት ግዢን በተመለከተ ፈላጊው አካል ወይም ግለሰብ መኖሪያ አካባቢው ወይም ሀገሩ የእርስዎ ለሽያጭ የተዘጋጁ ቤቶች ካሉበት ስፍራ የተራራቀ የሚሆንበት አጋጣሚ አለ። ከዚያ በተጨማሪም ገዢው ያለው የተጣበበ ጊዜ በአካል ተገኝቶ ቤቶቹን እንዳይመለከት እንቅፋት የሚሆንበት አጋጣሚም የተለመደ ነው። በእንደዚህ አይነቱ ጊዜ አካላዊ ያልሆኑ የቤት ጉብኝቶች መርሃ ግብሮችን በተለያዩ የዲጂታል አማራጮች በመጠቀም ማሰናዳት የሚቻል ሲሆን ለደንበኞች ብቻ ሳይሆን ለኩባንያዎም ስራዎችን የማቅለል አጋጣሚ ይፈጥራል። የቤቶቹን ውስጣዊ እና ውጫዊ ክፍል ፣ የአሰራር ዲዛይኑን ፣ የተማሉለትን መሰረተ ልማቶች እና የመሳሰሉትን ገዢዎች ባሉበት ስፍራ ሆነው በቪዲዮ እንዲመለከቱ ዕድል መፍጠር ይቻላል።

የውጤታማነት ማረጋገጫዎች

ኩባንያዎ ለደንበኞቹ ከህልማቸው ጋር የሚያገናኛቸውን ምርጥ ቤት እንደሚያዘጋጅ የሚገልፁ ድንቅ ድንቅ ማስታወቂያዎችን ሊሰራ ይችላል። ሆኖም ይህ ሁሉ ከእርስዎ ከጉዳዩ ባለአንደኛ ወገን የሚወጣ መልዕክት እንደመሆኑ ሙሉ እምነትን ያገኛል ብሎ ማሰብ ያዳግታል። ስለዚህ ከዚህ ቀደም የእርስዎን ኩባንያ ግልጋሎት ያገኙ ግለሰቦችን ምስክርነት በዲጂታል አማራጮችዎ ማካተት እጅግ ጠቃሚ ውጤት አለው። ከተቋምዎ ቤቶችን የገዙ ሰዎችን ምስክርነት በፎቶዎች በታጀቡ ፅሑፎች ፣ ወይም በቪዲዮ መልክ በማዘጋጀት የእርስዎ የሪል ስቴት ኩባንያ ቃል የገባውን የመፈፀም የስኬት ታሪክ ያለው መሆኑን ማስረገጥ ወሳኝ ነው። ከደንበኞች ሀሳብ በተጨማሪ ተቋምዎ ከዚህ በፊት ያገኛቸው ሽልማቶች እና የምስክር ወረቀቶች ካሉም በዲጂታል አማራጮችዎ በሚገባ ማስተዋወቅ ለአዳዲስ ደንበኞች የመተማመን ስሜትን ማሳደጉ እሙን ነው።

በመጨረሻም በዲጂታል ማርኬቲንጉ ላይ የተደራጀ እና በመስኩ የተመሰገነ ቡድን ያለውን ዋፋ ማርኬቲንግ እና ፕሮሞሽንን ከጎን አሰልፎ ወደመስኩ መግባት ለተሻለ ውጤታማነት እንደሚያበቃ ለመጠቆም እንወዳለን።

 

 

 

 

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top