የማርኬቲንግ የለውጥ ጉዞ
ዓለማችን ከጋርዮሽ ዘመን ጀምሮ እስከአሁኑ የቴክኖሎጂ ዘመን በተለያዩ የለውጥ ሂደቶች እንደማለፏ ሁሉ ማርኬቲንጉም በለውጥ ሂደቱ ውስጥ አብሮ አልፏል። በዚህ ዘመን ምርትና አገልግሎትን ለማስተዋወቅ የምንጠቀምባቸውን በርካታ አማራጮች ያየ የቀደመውን ትውልድ የማርኬቲንግ ዘዴዎች መፈተሹ አይቀርም። የማርኬቲንጉ መስክ በክፍለ ዘመናት ውስጥ ሊታመን የማይችል ለውጥ አድርጓል። ዘመኑ የፈጠረውን የኢኮኖሚ ስርዓት እየተከተለ በየጊዜው የተጠቃሚና የደንበኞችን ፍላጎት በመቃኘት ራሱን እያሻሻለ የመጣው […]