እንኳን ደስ አለን!!! Leave a Comment / Uncategorized / By Wafa Digital እንኳን ደስ አለን!!! ‘The business excutive’ የተሰኘው አህጉር አቀፍ ተቋም ባዘጋጀው “የአመቱ የአፍሪካ ምርጥ ሴቶች” ሽልማት የድርጅታችን ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ፋንታዬ ጌታነህ በኢትየጵያ የማርኬቲንግና የፕሮሞሽን ዘርፍ ላበረከቱት አስተዋፅኦ ከአመቱ የአፍሪካ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶች ዝርዝር ውስጥ ተካተዋል። በዝርዝሩ ላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች የሆኑት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፣ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ እንዲሁም ዶ/ር ሊያ ታደሰ ይገኙበታል። ተቋማችን ለስራ አስኪያጃችን ወ/ሮ ፋንታዬ ፣ለመላው የዋፋ ማርኬቲንግና ፕሮሞሽን ሰራተኞች እንዲሁም ለዋፋ ደንበኞች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት ይወዳል። ዋፋ ማርኬቲንግና ፕሮሞሽን