ኤስኢኦ (SEO) ምንድንነው?

ዲጂታል ማርኬቲንግ በሁለት አበይት ክፍሎች የሚከፈል መስክ ነው። እነርሱም የክፍያ ዲጂታል ማርኬቲንግ(Paid digital marketing)  እና ኦርጋኒክ ዲጂታል ማርኬቲንግ ይባላሉ።

የክፍያ ዲጂታል ማርኬቲንግ ማለት በዲጂታሉ ዓለም የሚሰሯቸውን ማስታወቂያዎች ለድረ ገፆች በመክፈል ለተጠቃሚዎች እንዲደርሱ የሚያደርጉበት የማርኬቲንግ መንገድ ሲሆን ፤ ተፈጥሯዊ ዲጂታል ማርኬቲንግ (Organic digital marketing) ደግሞ የተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም ያለምንም ክፍያ በዲጂታል አማራጮች መልዕክት የሚያስተላልፉበት መንገድ ነው። ሁለቱም መንገዶች ስራዉን ለሚያከናውኑ ባለሙያዎች የተወሰነ ወጪ ሊያስወጡ እንደሚችሉ ግን ልብ ማለት ይገባል።

SEO (Search Engine Optimization )  ያለክፍያ ከሚከወኑ (Organic) የዲጂታል ማርኬቲንግ ስልቶች ዋነኛው ሲሆን ተጠቃሚዎች ከኢንተርኔት ላይ ምርትና አገልግሎት ሲያፈላልጉ  በቁልፍ ቃላት አማካኝነት የራስን ተቋም ምርት ወይም አገልግሎት ከፊት ለፊት እንዲያገኙ የሚያግዝ ስልት ነው።

Search engine optimization ከሁለት ቃላት የተገነባ ሲሆን ቃላቶቹም Search Engine እና Optimization ናቸው። Search Engine ማለት በኢንተርኔት አማካኝነት ሰዎች መረጃ ለማፈላለጊያነት እንዲጠቀሙት የተዘጋጀ መተግሪያ(Application )ወይም የኦንላይን ስርዓት (System ) ሲሆን ለዚህም ተጠቃሽ ምሳሌዎቹ ጎግል ክሮም (Google Chrome) ፣ ሞዚላ ፋየርፎክስ (Mozila Firefox) እና ያሁ ሰርች (YAHOO search) ናቸው። እነዚህ መረጃ ማፈላለጊያዎች ከተጠቃሚው የሚሰጣቸውን ቁልፍ ቃል (Key word) ይዘው ከዚያ ቃል ጋር የተያያዙ መረጃዎችን አስሰው በማውጣት ግልጋሎት ይሰጣሉ።

SEO የተመሰረተበት ሌላኛው የእንግሊዘኛ ቃል Optimization ሲሆን “ነገሮችን ወይም አቅሞችን በተሻለ እና ምርጥ በሆነ መንገድ አሟጥጦ መጠቀም” የሚለውን ትርጉም ይወክላል። ከሁለቱ ቃላቶች ጥምረት የተገነባው SEO – “በመረጃ ማፈላለጊያ መተግበሪያ ተቋምን ወይም ደግሞ ምርትና አገልግሎትን ለማስተዋወቅ አሟጥጦ የመጠቀም ሥርዓት ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።

ይህ ስልት በተለየ ሁኔታ ዌብሳይቶች ላይ የተሳካ ስራ የሚሰራበት የዲጂታል ማርኬቲንግ ዘርፍ ሲሆን በዌብሳይት ላይ የሚለጠፉ ልጥፎች (Contents) ውስጥ ወሳኝ የሚባሉ እና በብዛት ጥቅም ላይ የሚውሉ ቁልፍ ቃላትን በማስገባት ተገልጋዩ በእነዚህ መረጃ ማፈላለጊያ ገፆች ላይ ገብቶ ቁልፍ ቃላቶቹን በመጠቀም በሚያፈላልግበት ጊዜ የተቋምዎን ዌብሳይት ከፊት እንዲቀርብ የሚያደርጉበት ስልት ነው።

ተጠቃሚዎች በተለያዩ ምክንያቶች በእነዚህ እንደነጎግል ያሉ ማፈላለጊያዎች የተለያዩ ቁልፍ ቃላትን በማስገባት ፍለጋውን በሚያስጀምሩበት (Search –  በሚያደርጉበት) ጊዜ ከፊት ለፊት የሚመጡ የመጀመሪያ ደረጃ ያላቸው ውጤቶች በዚህ Search Engine optimization ትልቅ ስራ የሰሩ ዌብሳይቶች ናቸው።

                  SEO እንዴት እና ለምን አስፈለገ?

ዌብሳይትዎ ለምን ከፍተኛ SEO ደረጃ እንዲኖረው አስፈለገ? ይህን ጥያቄ ከመመለሳችን በፊት አንድ ጥያቄ በአክብርዎት እንጠይቅዎ። እርስዎ አንድ መረጃ በሚያፈላልጉበት ጊዜ ከሚመጣልዎ ውጤቶች ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃ ላይ ያሉትን ውጤቶች በምን ያህል መጠን ይከፍታሉ? የመጀመሪያ ደረጃ ላይ ያለው ውጤት ከሌሎቹ በተሻለ የሚፈልጉትን መረጃ ያካትታል ብለው ስለሚያስቡ ወደመጀመሪያው ውጤት ይሳባሉ አይደል? ይህ የመጀመሪያ ተመራጭ የሆነው ዌብሳይት በጥሩ ሁኔታ የተደራጀ SEO ያለው ነው።

ከፍተኛ SEO ያለው ድረ ገጽ እንዲኖርዎ ከፈለጉ ለድረ ገጽዎ እነዚህን ነገሮች ሊያሟሉለት ይገባል።

  • የሚያጋሯቸው ልጥፎች (Contents) በጥናት ያገኟቸውን ቁልፍ ቃላት ማካተት አለባቸው።
  • H1 Header ያላቸውን ርዕሶች ይጠቀሙ ( የድረ ገጽ ግንባታ ባለሙያዎች ይህንን በቀላሉ ይረዱታል።)
  • ተከታታይ ልጥፎችን ሊያጋሩ ይገባል።
  • የራስዎን ልጥፎች (Contents) እርስ በእርስ በማስፈንጠሪያዎች ያገናኙ።

በድረ ገጽ እና በዲጂታል ማርኬቲንጉ ላይ በጀማሪነት ደረጃ ላይ ያለ ተቋም ባለቤት ከሆኑ ወይም ደግሞ ከሌሎች ሥራዎችዎ ጋር ተደምሮ የሚኖርዎ ጊዜ ያነሰ ከሆነ የ SEO ደረጃው ከፍ ያለ ድረ ገጽ ባለቤት የመሆን ጉዳይ ሊያስጨንቅዎ እና ሊያሳስብዎ ይችላል። በዚህ ጊዜ በመስኩ የተካኑ ባለሙያዎችን እገዛ መጠቀም የብልህ ምርጫ ነው። በአገራችን ኢትዮጵያ የድርጅትዎ ድረ ገጽ የተሻለ SEO እንዲኖረው እንዲሁም በአጠቃላይ የዲጂታል ማርኬቲንጉ ዘርፍ ላይ መጠነ ሰፊ አቅም እንዲገነባ በመርዳቱ ረገድ ዋፋ ማርኬቲንግ እና ፕሮሞሽን ኃ/የተ/የግ/ማ ዝግጅቱን አጠናቅቆ ደንበኞቹን ለመርዳት ዝግጁ ነው። ኑ አብረውን ይስሩ፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top