የዌብሳይት ባለቤት የመሆን ጥቅም ምንድነዉ?

እየኖርንበት ባለው ዘመን ዓለም መዳፋችን ላይ ስትሆን፤መረጃ ደግሞ የጣቶቻችን ጫፍ ላይ ነዉ የሚገኘው። ይህ ሌላ ማብራርያ የማያስፈልገው ሀቅ ነው። መረጃዎችን ለመለዋወጥ ኢንተርኔት ከቀድሞው ባህላዊ የመረጃ ልውውጥ መንገድ ይልቅ ኢንተርኔት ከፍተኛ ብቃትና ፍጥነት አለዉ።

 ሰዎች አብዛኛውን የጊዜያቸዉን ክፍል  ኢንተርኔት ላይ  የሚያሳልፉበት የዲጂታል ዘመን ላይ እንገኛለን።  የተለያዩ ምርቶችን ለመግዛት አገልግሎት ለማግኘት የድረገፅ ፅሁፎችን ለማንበብ እራሳቸዉን ለማዝናናት ወዘተ ድረ ገጾችን ያስሳሉ፡፡

ይህንን የዘመናዊ ዓለም መገለጫ የተገነዘበው የቢዝነሱ ዓለምም  ንግዱን ወደ ኢንተርኔት አምጥቶታል።  በመሆኑም ወቅቱ ተቋማት ለደምበኞቻቸው እንደ መረጃ ምንጭ የሚጠቅም ዌብሳይት ካላዘጋጁ ወደኋላ እንዲቀሩ የሚያስገድድ ነው።

 

አንድ  ተቋም ደረጃውን የጠበቀ  ዌብሳይት ከሌለዉ  ሰፊ ጊዜያቸዉን ኢንተርኔት ላይ የሚያሳልፉ በርካታ ደምበኞችን ሊያጣ ይችላል ይህ ተቋም ስራውን  በፍጥነት የማሳደግ ፍላጎት ካለዉ ዌብሳይት የቢዝነስ ስኬት ላይ ምን አይነት ተፅዕኖ እያሳረፈ እንደሚገኝ  ማወቅ ይኖርበታል።

ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ነጥቦች ዌብሳይት ለተቋማት ቢዝነስ ምን አይነት አስተዋፆ እንዳለዉ ይጠቁማሉ።

1. ሁልጊዜ online መሆን

ማንኛዉም ግለሰብ ያሻዉ ቦታ ሆኖ ባሻው ሰዓት የድርጅቶችን ምርት እና አገልግሎት ከድረ ገጹ ማወቅ የሚችል ከመሆኑም በላይ ደምበኞች ከስራ ሰአት ዉጪ ቤታቸዉ ሆነዉ የሚፈልጉትን መረጃ እንዲያገኙ እና የሚፈልገጓቸውንም ምርቶች በሰለጠነ መንገድ እንዲገበያዩ ያስችላል።  

2. ደምበኞችን መርዳት

ከደንበኞች ጋር online መረጃን መለዋወጥ ቀላልና ገንዘብን ቆጣቢ ሲሆን በፍጥነት እና ግልፅ በሆነ መንገድ ምንፈልገውን መረጃ ለማስተላለፍ ያገለግላል። 50% በላይ የሚሆኑ ደምበኞች የሚፈልጉትን አገልግሎት ከማግኘታቸዉ በፊት የኢንተርኔት ገፅ ወይም ማህበራዊ ሚዲያን ይዳስሳሉ።

  ለምሳሌ ምርትዎንና የሚሰጡትን ወቅታዊ አገልግሎት ማስተዋወቅ ወደፊት ለመስራት ያሰቡትን ሁነት አስቀድሞ ለደምበኞች ማሳወቅ ደንበኞች ራሳቸውን ለተሳታፊነት ወይም ለተጠቃሚነት ቀድመው እንዲያዘጋጁ መንገድ ይከፍታል

3. ጥሩ ስምና ታማኝነትን መጎናፀፍ

አባቶቻችን  በድሮ ጊዜ   አንድን ድርጅት ለማመን ስልክ ቁጥርና አድራሻ እንደ ግዴታ እንደሚያዩ  ሁሉ የዘመኑ ትዉልድ ደግሞ የግል ዌብሳይትና ማህበራዊ ሚዲያቸዉን ማየት ይፈልጋል። ይህ የደምበኞችን ታማኝነት ለማግኘት መሰረታዊ ነገር ነዉ የአንድ ተቋም ዌብሳይት ማራኪ እና ላጠቃቀም ምቹ ከሆነ ደምበኞች ወደ ማመን ያጋድላሉ። አንድ ተቋም የተደራጀ ድረ ገጽ እና የማህበራዊ ትስስር ገጽ ሲኖረው ተመልካቹ የዛን ተቋም የተደራጀ መዋቅር የመረዳት ስነ ልቦና ይፈጠርበታል፡፡

4. የኘሮፌሽናል ዌብሳይት ባለቤት መሆን የሚፈጥረው ተጽዕኖ

የተለያዩ ተቋማትን ዌብሳይትና ማህበራዊ ሚዲያን በሚዳስሱ ግለሰቦች ላይ ተቋሙ ተፅዕኖ ካላሳደረ  ዌብሳይቱን ደጋግመዉ የሚጎበኙበት ሌላ ምክንያት ስለማይኖራቸው  በተለያየ መንገድ ትኩረታቸውን መሳብ አለበት፡፡  የእርስዎ ዌብሳይት ተመልካቾችን የሚማርክ አይነት ካልሆነ በድጋሚ ወደገጹ የሚሳቡበትን ምክንያትና ፍላጎት ያጣሉ ስለዚህ የአንድ የድርጅትዎን ዌብሳይት በደረጃው ላቅ ያለ በማድረግ በሌሎች ተፎካካሪ ተቋማት ድረ ገጽ ጥራት የተሰላቸውን ደንበኛ ወደእርስዎ ተቋም መሳብ ይችላሉ፡፡

5. ብልህነት ነው፡፡

በዌብሳይት ታግዘዉ የሚሰሩ ከሆነ የምርትዎን ተደራሽነት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከማረግ ባሻገር ንግድዎ በእጥፍ ድርብ እንዲጨምር ይረዳል በተጨማሪም ምርትና አገልግሎትዎ አከባቢ ላይ ያሉ በርካታ ማነቆዎችን አልፎ በጥሩ ሁኔታ አንዲስፋፋ ዌብሳይት ጉልህ አስተዋጽኦ አለዉ

6. ገቢ ለማምጣት

የእርስዎ ዌብሳይት በአለም ዓቀፍ ደረጃ በብዛት የሚጎበኝ ከሆነ በዚያ ብቻ ተጨማሪ ገቢ የሚያገኙበትን መንገድ ዘመናዊው የዲጂታል ዓለም ይፈቅዳል ይህም  ዌብሳይት ዲዛይን ሲያስደርጉ የሌሎች ድርጅቶች ማስታወቂያ የሚለቀቅበት  ቦታ (ads ) እንዲኖረው በማድረግ ተጨማሪ ገቢ መፍጠር ይችላሉ

7. እራስን ማስተዋወቅ

ዌብሳይት ለተቋማት እንደ መደብር ቢሮ እና ማሳያ ክፍል ሊያገለግል ይችላል በትንሽ ጊዜና ዋጋ የስራ ክፍል አድራሻ እና ለሽያጭ የሚቀርቡ ምርቶችን በተፈለገ መልክ አስተዋውቀው ባጭር  ጊዜ ወደ ስራ እንዲገቡ ይረዳል

8. ልምድዎን ማካፈል

 

የአንድ ድርጅት ዌብሳይት በሚሰጠዉ አገልግሎትና በሚሸጠዉ ምርት ላይ ብቻ ሊገደብ አይገባም ያለዉንም ልምድ ለማህበረሰቡ ማካፈል አለበት ለምሳሌ አንድ  የአስጎብኚነት አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም አንድን ቤተሰብ ወይንም ቡድን ከምዝገባ ክንውንና ትኬት መቁረጥ ጀምሮ መዳረሻዉ ለይ ደርሶ  ተዝናንቶ እና ጉብኝቱን አገባዶ እስኪመለስ ድረስ ላለዉ ሂደት ዶክመንተሪ ሰርቶ ዌብሳይት ላይ በማስቀመጥ  ተቋሙ በተዘዋዋሪ የታማኝነት ደረጃውን የሚጨምር  ሲሆን በዛዉ ልክ አዳዲስ ደምበኞችንም ያፈራ ዘንድ ይረዳዋል

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top