6ኛው የኢትዮ – USA የንግድና የኢንቨስትመንት ፎረም

6ኛው የኢትዮ - USA የንግድና የኢንቨስትመንት ፎረም

ዋፋ ማርኬቲንግና ፕሮሞሽን ያዘጋጀው 6ኛው የኢትዮ – USA የንግድና የኢንቨስትመንት ፎረም የፊታችን ረቡዕ ሚያዝያ 4/2015 በዋሽንግተን ዲሲ ይካሄዳል።

ዋፋ ማርኬቲንግና  ፕሮሞሽን ከውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ፣ በዋሽንግተን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፣ በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ  እንዲሁም ከ CCA (Corporate Commission on Africa) ጋር በጥምረት የሚያዘጋጀው ፎረሙ የኢትዮጵያ እና የአሜሪካ የንግድ ማህበረሰብ እና ባለሀብቶች እንዲሁም ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች የሚሳተፉበት ሲሆን ለሀገራችን ከፍተኛ ፋይዳ እንደሚኖረው ይጠበቃል።

ከኢትዮጵያ በፎረሙ ለመሳተፍ የሚጓዘውን ቡድን የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር አህመድ ሺዴ የሚመሩት ሲሆን የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት ዕድሎች የተመለከተ ማብራሪያ በኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ወ/ሮ ሌሊሴ ኔሜ ይቀርባል።

ዋፋ ማርኬቲንግና ፕሮሞሽን ከዚህ ቀደም በተለያዩ ሀገራት ተመሳሳይ የንግድና የኢንቨስትመንት ፎረሞችን ማዘጋጀቱ ሲታወስ በዚህም ለኢትዮጵያ በርካታ ዕድሎች እንዲፈጠሩ የበኩሉን አስተዋፅኦ በማበርከት ላይ ይገኛል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top