ዓለም አቀፍ የአበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ አውደ ርዕይ በአዲስ አበባ ይካሄዳል

 

ዓለም አቀፍ የአበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ አውደ ርዕይ በአዲስ አበባ ይካሄዳል

ጥር8/2010

    ዓለም አቀፉ የአበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ አውደ ርዕይ በሚቀጥለው ወር በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው። የኢትዮጵያ ሆርቲካልቸር አምራች ላኪዎች ማህበር አውደ ርዕዩን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ፥ በአውደ ርዕዩ ላይ ለመሳተፍ 120 የሀገር ውስጥና የውጭ አምራቾች ይገኙበታል ብሏል።እንዲሁም የግብዓት አቅራቢዎች፣ አማካሪዎች፣ ገዥዎችና ባለድርሻአካላት መመዘገባቸውን ማህበሩ ገልጿል።

ከአውስትራልያ፣ ከጃፓን፣ ከአሜሪካ፣ ከደቡብ ኮሪያ፣ ከአውሮፓ፣ ከመካከለኛው ምሥራቅ፣ ከአፍሪካ አገሮች በአጠቃላይ ከ40 ሀገራት በላይ የተወጣጡ ተሳታፊዎች በአውደ ርዕዩ ላይ ይሳተፋሉ።የአውደ ርዕዩ መካሄድ ኢትዮጵያ በዘርፉ ያላትን እምቅ አቅም ከማሳየት ባለፈ አገሪቷ በመስኩ ተሰማርተው የሚገኙ ኩባንያዎች ልምድ እንዲቀስሙ እድል እንደሚፈጥር ይጠበቃል። ከዚህ ባለፈ በመንግስት የተለዩ አዳዲስ የኢንቨስትመንት ቦታዎች ለዓለም አቀፉ ተዋንያኖች ለማስተዋወቅ መልካም አጋጣሚ ይሆናል መባሉን ኢዜአ ዘግቧል።

Log in

Contact us

Wafa Marketing & Promotion PLC

Mexico Biftu Building 8th & 11th Floor ,

In front of Addis Ababa University School Of Commerce

Addis Ababa, Ethiopia

Phone: +(251) 115 525031

JoomShaper