• 0.gif
  • 1.gif
  • 2.gif
  • Facebook Page: 180145508726198
  • Flickr: wafa_marketing__promotion_plc
  • YouTube: wafa360

የኢትዮ - ጃፓን ንግድና ኢንቨስትመንት ፎረም በቶኪዮ- ጃፓን ሊካሄድ ነው።

Print
PDF

ዋፋ ማርኬቲንግና ፕሮሞሽን .የተ.የግ.ማህበር... ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፣ ከጄትሮ እንዲሁም በጃፓን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር በመተባበር ግንቦት 25,2005 . በጃፓን ዋና ከተማ ቶኪዮ የንግድና ኢንቨስትመንት ፎረም ሊያካሄዱ ነው።

የንግድና ኢንቨስትመንት ፎረሙ ኢትዮጵያ በቡና፣ በአበባ ምርት፣በጥራጥሬና የቅባት እህሎች እና በቆዳና ሌጦ ከጃፓን ጋር ያላትን የውጭ ንግድ በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያጠናክረው የተገመተ ሲሆን 45 በላይ በዘርፉ የተሰማሩ ኢትዮጵያውያን ባለሃብቶች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።

በኢትዮ- ጃፓን ንግድና ኢንቨስትመንት ፎረም የተለያዩ የመንግስትና የግል የንግዱ ማህበረሰብ አካላትንደሚገኙ ይጠበቃል

Ethio-Japan Trade and Investment forum will be held in Tokyo-Japan.

Print
PDF

WAFA Marketing & Promotion plc is joining hands with FDRE Ministry of Foreign Affairs, Jetro and The Japanese Embassy in Ethiopia   in organizing a trade and investment forum in Tokyo, Japan on June 2, 2013.

The Trade and Investment Forum will strengthen the tie that Ethiopia has with Japan with regards to foreign trade especially in the areas of coffee, floriculture, grains, oilseeds and leather products.

More than 45 Ethiopian Investors who are operating in these areas are expected to participate in the forum.

Flights to boost Korea-Ethiopia ties

Print
PDF

Ethiopia’s flag carrier’s decision to launch flights to Korea is more than just commercial interest, said the African country’s ambassador to Seoul.

“It is an expression of our solidarity,” Ambassador Dibaba Abdetta told The Korea Times on May 8 in his Itaewon office.

On June 19, Ethiopian Airlines’ first passenger flight will land at Incheon International Airport, making it the first African airline company to operate a route to Korea. Four flights will fly to Addis Ababa, the capital, every week with a 45-minute stop in Hong Kong for refueling.

This is part of the Ethiopian flag carrier’s investment in the rising market in Asia. Soon, it will add the Philippines on its destination list as well. New Delhi, Hong Kong, Beijing, Guangzhou and Hangzhou are among existing destinations in Asia.

Ethiopian Airlines is among the biggest carriers in Africa, servicing 30 countries around the world and 40 destinations on the African continent.

Asked about competition with Korean Air, the ambassador said that the operation of the two different carriers will only be complementary. Last year, Korean Air began a direct flight service to Nairobi, the capital of Kenya, but it is reportedly not making money.

Abdetta highly regards the 50 years of diplomatic relations between the two countries and Ethiopia’s dispatch of soldiers during the 1950-53 Korean War.

Korea and Ethiopia established the diplomatic ties in December 1963, but the Korean War is what set the tone of the entire relationship.

Read more...

የኢትዮ - ደቡብ ኮርያ ንግድና ኢንቨስትመንት ፎርም ጁን 19,2013 ይካሄዳል።

Print
PDF

  • የኢትዮ ኮርያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረበት 50ኛ ዓመት ይከበራል
  • የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሴዑል ኮርያ የቀጥታ በረራውን ይጀምራል

በደቡብ ኮሪያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አዘጋጅነት፤ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከኤዤያና ኦሺኒያ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት፣ ከቢዝነስ ዲኘሎማሲ ዳይሬክቶሬት ጄኔራል፣ ከዋፋ ማርኬቲንግና ፕሮሞሽን እና ከሌሎች ተባባሪ ኩባንያዎች ጋር በመሆን የኢትዮ-ደቡብ ኩሪያ ንግድና ኢንቨስትመት ፎረም ጁን 19/2013 ሊካሄድ ነው፡፡

 

ለኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ የሚገኘው የኤ.ፌ.ዲ.ሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በፎረሙ የኢትዮጵያን እምቅ ሃብቶችና የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለደቡብ ኮርያ አቻው የሚያስተዋውቅ ሲሆን በፎረሙ የተለያዩ የንግድና ግብርና ምርቶች ዘርፍ የተሰማሩ ኢትዮጵያውያን ባለሃብቶች ፣ ከአስራ አምስት በላይ የመንግስትና የግል ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚገንኙበት ይጠበቃል።

ከኢትዮ - ሳውዝ ኮሪያ ንግድና ኢንቨስትመንት ፎረም ጎን ለጎን ኢትዮጵያና ደቡብ ኮሪያ የዲፕሎማቲክ ግንኙነት የጀመሩበትን 50ኛ ዓመት ሲያከብሩ ጁን 18,2013 የኢትዮጵየ አየር መንገድ ከ አ/አበባ ወደ ሴዑል ኮርያ ቀጥታ በረራ እንደሚጀምር ታውቋል።

በዚህ ፎረም ላይ የተለያዩ የመንግስትና የንግዱ ማህበረሰብ አካላት ተሳታፊ ይሆናሉ።

Ethio-South Korea Investment forum will take place on June 19, 2013.

Print
PDF

· The 50th Anniversary of Ethio - South Korea Diplomatic Relationship will be celebrated

· Ethiopian Airlines will start a direct route flight to Seoul, South Korea

South-Korean Embassy in Ethiopia , FDRE Ministry of Foreign Affairs, Asia & Oceania Affairs Directorate, Business Diplomacy Directorate General and others are teaming up with WAFA Marketing and Promotion plc to organize the Ethio-South Korea Trade and Investment Forum on June 19,2013.

During the forum, the Ministry of Foreign Affairs, which is giving a special focus to Economic Diplomacy, will promote Ethiopia’s great resource potential and investment opportunities to its South Korean peer.

Ethiopian Investors from various trade and agriculture sectors as well as more than 15 governmental and private university representatives are expected to participate during the forum.

Apart from the Ethio-South Korea forum, Ethiopia and South Korea will be celebrating the 50th anniversary of diplomatic relationship between the two nations. Furthermore Ethiopian Airlines will be starting a direct flight from Addis Ababa to Seoul on June 18th, 2013.

Governmental & non-governmental organizations and Investors will participate in this event.

በኢንቨስትመንት አዋጭነት ጥናት ላይ ያነጣጠረው ተቋም

Print
PDF

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከመነቃቃት አልፎ፣ ዕድገት እያስመዘገበ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ የአገሪቱ ኢኮኖሚ በተለያየ መስክ ዕድገት እየተመዘገበበት ይገኛል፡፡ ከእነዚህም መስኮች አንዱ የወጭ ንግድ ዘርፍ ነው፡፡

ምንጭ፥ ሪፖርተር ጋዜጣ

 

የወጭ ንግድ ዘርፍ በየዓመቱ ዕድገት እያስመዘገበ ቢሆንም አገሪቱ ካላት እምቅ ሀብት አንፃር ዕድገቱ ብዙም የሚጠበቀውን ያህል አልሆነም፡፡ የወጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ዕድገት ቢያሳይም የሚጠበቀውን ያህል ግን አይደለም፡፡ የወጭ ንግድ ዘርፍን በዋነኛነት የተሸከመው የግሉ ዘርፍ ሲሆን፣ ዘርፉ ከተፈጠረ ከሁለት አሠርታት የዘለለ ባለመሆኑ ድጋፍ እንደሚያስፈልገው አይካድም፡፡

በተለይ የወጭ ንግድ ምርቶችን መዳረሻዎችን ከማስፋት በተጨማሪ የውጪ ዓለም ስለኢትዮጵያና ስለኢትዮጵያ ምርቶች ግንዛቤ እንዲያገኝ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ በዋነኝነት ይህንን ክፍተት ለመድፈን፣ ብሎም የአገር ውስጥ ምርቶች ብራንድ (መለያ) እንዲኖራቸው፣ ብራንዳቸውም ተለይቶ እንዲታወቅ ለማድረግና ፋይዳ ያላቸውን ዝግጅቶች ለማዘጋጀት ዋፋ ማርኬቲንግና ፕሮሞሽን ድርጅት ተቋቁሟል፡፡ ኩባንያው ከተመሠረተ ጀምሮ ያከናወናቸው ሥራዎችንና በቀጣይነት ስለሚያካሒዳቸው ተግባራት ውድነህ ዘነበ የዋፋ ማርኬቲንግና ፕሮሞሽን ኩባንያ ዋና ሥራ አስኪያጅ ወይዘሮ ፋንታዬ ጌታነህን አነጋግሯቸዋል፡፡

ሪፖርተር፡- ዋፋ ማርኬቲንግና ፕሮሞችን መቼና ለምን ተቋቋመ?

/ ፋንታዬ- ዋፋ ማርኬቲንግና ፕሮሞሽን ኩባንያ 2001 .. ነው የተቋቋመው፡፡ ኩባንያው በዋናነት ሦስት ነገሮችን ይዞ ነው የተቋቋመው፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ዓለም አቀፍና አገር አቀፍ ዝግጅቶች ማዘጋጀት፣ በማስታወቂያ ደረጃ ደግሞ ብራንዲንግ ማድረግ በሌላ በኩል በሲኒማውም ዘርፍ በተወሰነ ደረጃ የመግባት ፍላጎት አለን፡፡ በዋነኛነት ግን ዓለም አቀፍና አገር አቀፍ ዝግጅቶችን ማዘጋጀት ላይ እናተኩራለን፡፡

ሪፖርተር፡- ዓለም አቀፍ ዝግጅቶችን ሲባል ምን ዓይነት ሥራዎችን ያካትታል?

/ ፋንታዬ- አገራችን የውጭ ባለሀብቶችን የመሳብ ፍላጎት አላት፡፡ እስካሁን ባሉት ጊዜያት በቂ የሚባል ባለሀብት ወደ አገር ውስጥ አልገባም፡፡ የውጭ ባለሀብቶችም በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሥራ ውስጥ በሰፊው እንዲገቡ የምንሠራው ሥራ አለ፡፡ ሁለተኛው ቱሪዝም ላይ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ከበርካታ አገሮች ጋር ስትነፃፀር የተሻለ የቱሪዝም መስህብ ቢኖራትም፣ ከዘርፉ የምታገኘው ገቢ ደግሞ አነስተኛ ነው፡፡ ስለዚህ በቱሪዝም ዘርፍ የአገራችንን መልካም ገፅታ እንገነባለን፡፡ ኢትዮጵያ ረዥም ዓመት በድርቅና ረሀብ ትታወቃለች፡፡ ይህንን በመፋቅ አገራችን ያሏትን ሀብቶች በማስተዋወቅ የውጭ ቀጥተኛ መዋለ ንዋይ ፍሰቱ እንዲጨምር እንሠራለን፡፡ እስካሁን አሜሪካ ሁለት ጊዜ ዓለም አቀፍ ኢቨንት (ሁነት) አዘጋጅተናል፡፡ እንግሊዝ፣ ጣልያን፣ ሕንድ፣ ሩስያ በቅርቡ ደግሞ ጃፓንና ደቡብ ኮርያ ዝግጅት እናካሒዳለን፡፡

ሪፖርተር፡- ከዚህ ሥራችሁ ምን ውጤት ተገኘ?

/ ፋንታዬ- እስካሁን ድረስ በእነዚህ አገሮች ውስጥ ባካሄድናቸው የተለያዩ ዝግጅቶች ከሁለት ሺሕ በላይ ባለሀብቶች አግኝተናል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ ወደ አገር ውስጥ መጥተዋል፡፡ ባለሀብቶች የመጡት አንድም ኢንቨስት ለማድረግ፣ ሁለትም ለመጎብኘት ነው፡፡ ይሄ ለአገራችን የሚሰጠው ጠቀሜታ ቀላል አይደለም፡፡ እንገፋበታለን፡፡

ሪፖርተር፡- ምን ዓይነት ምርቶችን ነው በውጭ አገር የምታስተዋውቁት?

/ ፋንታዬ- አንድ የኢንቨስትመንት ፎረም ለማዘጋጀት ከአራት እስከ ስድስት ወር ይፈጅብናል፡፡ ይህ ፎረም ምንድነው የሚያካትተው? በመጀመርያ በፎረሞቹ ላይ 70 በመቶ የሚሆነውን የግሉ ዘርፍ እናሳትፋለን፡፡ ለምሳሌ ፎረሙ የሚካሄደው ሩስያ፣ ሞስኮ ከሆነ የሞስኮ ፍላጎት ምንድነው? የሚለውን እናጠናለን፡፡ የግብርና ምርት ነው ወይ? ማዕድን ነው ወይ? ማኑፋክቸሪንግ ነው ወይ? የሚለውን እናጠናለን፡፡ በጥናታችን መሠረት የተሠማሩ የግሉ ዘርፍ ተዋናዮችን እናሳትፋለን፡፡ በዚህም ከፍተኛ ውጤት ታይቷል፡፡ ለምሳሌ በሞስኮ የደራ የአበባ ገበያ አለ፡፡

የኢትዮጵያ አበባ ሞስኮ የሚሸጠው ከሌላው አገር ገበያ ነው፡፡ ሞስኮ ላይ ፕሮግራም ካዘጋጀን በኋላ በዚህ ሳምንት መጀመርያ የሞስኮ ባለሀብት በቀጥታ የኢትዮጵያን አበባ ከኢትዮጵያ ለመውሰድ የሚያስችለውን ስምምነት ለማድረግ አዲስ አበባ መጥቷል፡፡ ባለሀብቱ ከአበባ ዘርፍ ተዋናዮች ከንግድ ሚኒስቴርና ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ድርድሩን አካሂዷል፡፡ ይህ ማለት በሚቀጥሉት ጊዜያት የኢትዮጵያ አበባ በቀጥታ ሞስኮ ይሄዳል ማለት ነው፡፡

ሪፖርተር፡- በውጭ አገር የዚህ ዓይነት ዝግጀቶች ከተካሄዱ በኋላ የሚመጡ ኢንቨስተሮችን በማስተናገድ በኩል አለመናበብ እንዳለ ይነገራል፡፡ እናንተ ይህንን ችግር አስተውላችሁታል?

/ ፋንታዬ- አንዱና ትልቁ ችግር የሆነው እኛ ኢንቨስትመንት ፎረሙን አካሂደን እንመጣለን፡፡ ከመጣን በኋላ ኢንቨስተሮቹ ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ፡፡ ኢትዮጵያ ከመጡ በኋላ ማነው የሚያገኛቸው? የሚያገኛቸው ደላላ ነው፡፡ አንዳንድ ቦታ እንዲሁም ባለሀብቶቹ ኢንቨስት ሲያደርጉ 30 በመቶ ድርሻ ለደላላው መስጠት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ብዙ ዓይነት መዘበራረቅ አለ፡፡ ሁለተኛ ደግሞ ኢንቨስተሮቹ ከፎረሙ በኋላ ወዲያውኑ ቢመጡ ምንድነው የምንሰጣቸው፡፡ የተጨበጠ ፕሮጀክት አለን ወይ? ፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ የትኞቹ የልማት ድርጅቶች ነው የሚሸጠው? በስንት ብር? የሚሉት ነጥቦች አልተመለሱም ነበር፡፡ እኛ ኢንቨስትመንት ፎረሙን አካሂደን እንመጣለን፡፡

ኢንቨስተሮቹ ይመጣሉ፡፡ አንዴ ውጭ ጉዳይ፣ አንዴ ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ፣ አንዴ ንግድ ሚኒስቴር ይሄዳሉ፡፡ አንዳንዶቹ ተንከራተው ተስፋ ቆርጠው ወደ አገራቸው ይመለሳሉ፡፡ አንዳንዶቹ ተሳክቶላቸው ይሠራሉ፡፡ መናበብ ያስፈልጋል፡፡ እኛ እየሞከርን ያለነው ኢንቨስትመንት ፎረሙን ካካሄድን በኋላ የሚመጡ ባለሀብቶች እኛ በቀጥታ እንዲመጡ፣ ከዚያ በኋላ የማስተባበሩን ሥራ እንድንሠራ ነው፡፡ ከዚያ በኋላ የአዋጭነት ጥናት እንሠራላቸዋለን፡፡ ኢንቨስትመንት ፈቃድ እናወጣላቸዋለን፡፡ የሚያስፈልጓቸውን ሥራዎች በተቀላጠፈ መንገድ እናከናውንላቸዋለን፡፡ እያንዳንዱ ጠብታ ገንዘብ ለመንግሥት ይገባል፡፡ አሁን ይህንን ለመሥራት አቅደናል፡፡

ሪፖርተር፡- ይህ ማለት አንድ ኢንቨስተር ከውጭ እንደመጣ ከናንተ ጋር እንዲገናኝ ሆኖ፣ እናንተ የአዋጭነት ጥናት ሠርታችሁለት ብሎም ሌሎችን ሥራዎች ሠርታችሁለት ወደ ኢንቨስትመንት እንዲገባ ማስቻል ማለት ነው?

/ ፋንታዬ- እኛ አሁን ወደዛ ነው እየሄድን ያለነው፡፡ አሁን በዋነኛነት ፕሮግራሞችን እናዘጋጃለን፡፡ የአዋጭነት (የፊዚቢሊቲ) ሥራዎችን እንደምንሠራ ሆነን ነው የተቋቋምነው፡፡ ዋፋ ሦስት ዳይሬክተር ነው ያለው፡፡ አንደኛው ብራንድና ማስታወቂያ ነው፡፡ ሁለተኛ አስተዳደርና ፋይናንስ ነው፡፡ ሦስተኛው ኢንተርናሽናል ኢቨንት ነው፡፡ በኢንተርናሽናል ኢቨንት ውስጥ ኢንቨስተር ሪሌሽንና ፕሮሞሽን የሚባል አለን፡፡ ይህንን ሥራ እንድንሠራ ከመጀመርያ ጀምሮ ነው የተቋቋምነው፡፡

ሪፖርተር፡- ብዙ ዓይነት ኢንቨስትመንት አለ፡፡ ግብርና፣ ማይኒንግ፣ ማኒፋክቸሪንግ ተጠቃሾች ናቸው፡፡ ዋፋ እነዚህን የተለያዩ ዘርፎች የአዋጭነት ጥናት ሊሠራ የሚያስችል አቅም አለው?

/ ፋንታዬ- የምንሠራው ዋናው ሥራችን ይኼ ይሆናል፡፡ ሁለተኛ ሥራ በጋራ ይሠራል፡፡ ሁሉንም ባለሙያ አትቀጥረውም፡፡ አውት ሶርስ ታደርጋለህ፡፡ በማዕከል ደረጃ የተወሰነ ብቃት ያለው ባለሙያ ይዘህ ለሌሎቹ ሥራውን ትሰጣለህ፡፡

Read more...

የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ የኢትዮጵያ አምባሳደሮች ከዋፋ ማርኬቲንግና ኘሮሞሽንና ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አደረጉ

Print
PDF

የኢ... የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከዋፋ ማርኬቲንግና ኘሮሞሽን ጋር በጋራ በመተባበር የተለያዩ የውጪ የንግድና ኢንቨስትንትና ፎረሞችን ማዘጋጀታቸው ይታወሳል፡፡ ኢትዮጵያ በንግድ በኢንቨስትመንትና በቱሪዝም ያላትን አቅም ለውጭው አለም በማስተዋወቅና የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን ወደ ሀገር ወስጥ ከመሳብ አኳያ የተዘጋጁት ፎረሞች አይነተኛ ሚና ተጫውተዋል፡፡

በመሆኑም አገራችን ኢትዮጵያ በንግድ፣ በቱሪዝም እና በኢንቨስትመንት ያሏትን አቅሞች በበለጠ ለውጪው አለም ለማስተዋወቅ እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ከኢ... የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር ተቀራርበው ሰፊ ሀሳቦችን እንዲለዋወጡበት ያመች ዘንድ መጋቢት 27 ቀን 2005 . ዋፋ ማኬቲንግና ፕሮሞሽን ከውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በሸራተን አዲስ ላሊበላ አዳራሽ የምክክር መድረክ አካሄዷል፡፡ በምክክር መድረኩ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር / ቴዎድሮስ አድሓኖም፣ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች የተሠማሩ ባለድርሻ አካላት እንዲሁም ከተለያዩ ሀገራት የመጡ የኢትዮጵያ አምባሳደሮችና ቆንስላዎች ተገኝተዋል፡፡

ዋፋ ማርኬቲንግና ኘሮሞሽን ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የኢትዮ-ሩሲያ የንግድና ኢንቨስትመንት ፎረም በሞስኮ ተካሄደ።

Print
PDF

ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን ጨምሮ ከ60 በላይ በጥራጥሬ፣ በአበባ፣ በቆዳና

ሌዘር እንዲሁም በተለያዩ የኢንዱስትሪ ዘርፎች የተሠማሩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ

ያልሆኑ ተቋማት የተሳተፉበት የኢትዮ- ሩሲያ የንግድና ኢንቨስትመንት ፎረም የካቲት 26 2005 ዓ.ም በሩሲያ ዋና ከተማ ሞስኮ  ተካሄደ ፡፡

 

ፎረሙ የረዥም ጊዜ የታሪክና የዲኘሎማሲ ግንኙነት ያላቸው ኢትዮጵያና ሩሲያ በንግድና ኢንቨስትመንት እንዲሁም በቴክኖሎጂ ሽግግር የበለጠ ግንኙነት ያዳበሩበት እና ሩሲያዊያን ባለሀብቶች በኢትዮጵያ የተለያዩ የኢንቨስትመንት ሴክተሮች ኢንቨስት እንዲያደርጉና በግብርና እና ሆርቲካልቸር ዘርፎች የተሠማሩ ኢትዮጵያዊያን ባለሀብቶች ደግሞ በሩሲያ የንግድ ግንኙነት እንዲፈጥሩ አግዟል፡፡

የኢትዮ-ሩሲያ የንግድና ኢንቨስትመንት ፎረምን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አውሮፖ ዳይሬክቶሬት ጄኔራል እና በሩሲያ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር በጋራ በመተባበር የተዘጋጀ ሲሆን ከዚህ ቀድሞ በዘርፉ በህንድ- ኒውደልሂ፣በአሜሪካ-ዋሽንግተን፣ በጣሊያን-ሮም እንዲሁም እንግሊዝ-ሎንደን የተለያዩ የንግድና ኢንቨስትመንት ፎረሞችን በማዘጋጀት ከፍተኛ ልምድ ያለውና በዘርፉ ቀዳሚ ድርጅት የሆነው ዋፋ ማርኬቲንግና ኘሮሞሽን ኃ.የተ.የግ.ማህበር ነው፡፡

ይህንን ፎረም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አዳሃኖም እና የውሃና ኢነርጂ ማኒስትሩ አቶ አለማየሁ ተገኑ መርተውታል፡፡

The 1st Ethio-Russia Trade & Investment forum was held in Moscow,Russia..

Print
PDF

WAFA Marketing and Promotion Plc, in partnership with Federal Ministry of Foreign Affairs, Europe Directorate General, and the Ethiopian Embassy in Russia, organized the first Ethio-Russia Trade Investment Forum in Moscow March 5/2013.

The business forum showcase a new investment opportunities and potential Ethiopia has to offer to the international business communities. It also created  a platform for Ethiopian private sectors to establish business partnership and relationship with businesses(B to B) in Russia.

WAFA Marketing and promotion has organized similar forums successfully in the United States (2009 and 2011), United Kingdom, Italy and India.

This forum was lead by D.r Tewodros Adhanom, Ministry of foreign affairs and Mr Alemayehu Tegenu, Ministry of Water & Energy.

ዋፋ ከአዲስ አበባ መስተዳደር ጋር በመተባበር የአዲስ አበባን 125ኛ ዓመት በተለያዩ ዝግጅቶች አከበረ

Print
PDF

ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር በጥምረት ስራውን ያከናወነው ዋፋ በተለያዩ ዝግጅቶች

ፓናልና ሲምፖዚየሞች

ኤግዚቢሽንና ባዛሮች

ጥናታዊ ፊልምች

ማስታወቂያዎች

መጽሄቶች

የተለያዩ ስፖርታዊ ውድድሮች

የአዲስ አበባ ብራንድ ቀረፃ

የአዲስ አበባ እህት ከተሞች መካከል የፓናል ውይይቶችን

ድረ ገፅ ግንባታ እንዲሁም

የገቢ ማሰባሰብ ስራዎችን አከናውኗል።

የሀገሪቷንና የተለያዩ ድርጅቶችን ብራንድ የመቅረፅ እና ማስተዋወቅ ስራ እንዲሁም የተለያዩ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ሁነቶችንና ዝግጅቶችን ማቀላጠፍ ብሎም በስነጥበብ ዘርፍ (ስነ ፅሁፍ፣ቲያትር፣ ፊልም) ወዘተ ያለውን ልምድ በማምጣት እጅግ ስኬታማ የሆነ ዝግጅቶችን አከናውኗል።

WAFA Marketing & Promotion, in collaboration with Ethiopia Postal Service Enterprise, coordinated “the 8th African Postal Service Executives and senior officials conference”

Print
PDF


Addis Ababa, Ethiopia hosted the “8th African Postal Service Executives and Senior Officials Conference” in the ECA Hall, from July 4-10, 2012.  Ministers, CEO’s and Officials from 45 African countries, delegates from 56 countries who are active supporters of the union and over 500 participants are expected to attend this 10 days conference.

The mutual effort made by WAFA and Ethiopian Postal Service Enterprise, to advocate the positively changing aspects of Ethiopia to the delegated guests during their stay in Addis, is part of the image boosting campaign for “Branding Ethiopia to the World”. For more information please follow this link http://papuaddis.com/.

Meanwhile, the  organizers urged the Ethiopian Government and private companies to participate in sponsoring the event and contributes to its success. WAFA’s is commitment to make sure that this international event is undertaken with the utmost professionalism and embellished with the hospitality that we Ethiopians are famous for.