Category: Ethiopian News

ሩስያ በኢትዮጵያ የብረት ፋብሪካ ለማቋቋምና ልምዷን ማካፈል እንደምትፈልግ ገለጸች::

 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩስያ በዓለም ቀዳሚ ብረት አምራች ሀገር እንደሆነችና በኢትዮጵያ የብረት ፋብሪካ ለማቋቋምና ልምዷን ማካፈል እንደምትፈልግ ገለጸች። በሩስያ የብረት ማዕድን ጉዳዮች ተወካይ በሆኑት ሰሜኖቭ ቪክተር የተመራው ልዑክ ከኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ሚኒስትር መላኩ አለበል ጋር በአዲስ አበባ ተወያይተዋል፡፡ ሩስያ በዓለም ቀዳሚ ብረት አምራች ሀገር እንደሆነችና ኢኮኖሚዋም በዋናነት የሚመራው በብረት ወጪ ንግድ እንደሆነች ሰሜኖቭ […]

የዜጎችን የዲጂታል ክህሎት ለማሳደግ የሚያስችል ስምምነት ተደርገ

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ የተመድ የካፒታል ልማት ፈንድ እና የአለም አቀፉ የቢዝነስ ማሽን ኮርፖሬሽን የሴቶችና ወጣቶችን የዲጂታል እውቀት ለማሳደግ በኦንላይን ትምህርት መስክ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል።ስምምነቱ ሴቶችና ወጣቶች የራሳቸውን የቴክኖሎጂ መፍትሄ እንዲያፈልቁ፣ እንዲያሳድጉና ወደ ቢዝነስ እንዲቀይሩት ለማስቻል ነው።የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ፥ የዜጎችን የዲጂታል እውቀት ማሳደግ ለአካታች የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።የዜጎችን የዲጂታል […]

በዋፋ ማርኬቲንግ እና ፕሮሞሽን አስተባባሪት የተሰናዳው 9ኛው ሀገር አቀፍ የህብረት ስራ ማህበራት ሲምፖዚየም በአዲስ አበባ ከተማ ተካሄደ።

በሲምፖዚየሙ ላይ ከተለያዮ የሀገሪቱ ክፍል የመጡ የሸማቾች፣ የግብርና እንዲሁም የብድርና ቁጠባ ህብረት ስራ ማህበራት ዽሁፎችን በማቅረብ ልምዶቻቸውን አካፍለዋል።ከዚህ ባለፈም ጽሁፎቹ ሰፊ ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን ተሳታፊዎች ጥያቄና አስተያየታቸውን ሰንዝረዋል።የህብረት ስራ ማህበራት ያሉባቸው ተግዳሮቶች ሀላፊነቶች እና መፃኢ እቅዶችም ሰፊ ምክክር ተደርጓባቸዋል። የካቲት 2, 2014 ዓ.ም

በዋፋ ማርኬቲንግና ፕሮሞሽን አስተባባሪነት የተዘጋጀው 9ኛው ሀገር አቀፍ የህብረት ስራ ኤግዚብሽንና ባዛር በአዲስ አበባ ኤግዚቢሺን ማእከል በይፋ ተከፈተ።

በዋፋ ማርኬቲንግና ፕሮሞሽን አስተባባሪነት የተዘጋጀው 9ኛው ሀገር አቀፍ የህብረት ስራ ኤግዚብሽንና ባዛር በአዲስ አበባ ኤግዚቢሺን ማእከል በይፋ ተከፈተ።ኤግዚቢሽኑን አቶ ዳሪቦ ሁሴን የፌዴራል ህብረት ስራ ማህበራት ኮሚሽነር ዋና አማካሪ እንዲሁም አቶ አደም ኑሪ የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ሀላፊ በይፋ ከፍተውታል።የህበረት ስራ ማህበራት ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ የበኩላቸውን ያበረክቱ ዘንድ ሁሉም አካላት ሀላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ሲሉ አቶ አደም […]

በዋፋ ማርኬቲንግ እና ፕሮሞሽን አስተባባሪነት የተዘጋጀው የ9ኛው የህብረት ስራ ማህበራት ኤግዚቢሽንና ባዛር የቅስቀሳ የመኪና ትርዒት በደማቅ ሁኔታ ተካሄደ።

ከተለያዮ የህብረት ስራ ማህበራት ከአራቱም አቅጣጫ ተገኝተው ያደመቁት ትርዒቱ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት ፊት ለፊት መነሻውን አድርጎ በተለያዮ የከተማዋ አካባቢዎች ተካሂዷል።በተጨማሪም ከየካቲት 3 እስከ 7 በኤግዚቢሽን ማዕከል የሚካሄደው የህብረት ስራ ኤግዚቢሽን እና ባዛር በይፋ የተከፈተ ሲሆን በመርሀ ግብሩ ላይም የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ታድመውበታል።የኢግዚቢሽኑን በይፋ መከፈት ያበሰሩት የፊዴራል ህብረት ስራ ማህበራት ኮሚሽነር […]

35ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ ይጀመራል።

በጉባኤው ላይ ለመሳተፍም የህብረቱ አባል ሀገራት መሪዎች ዛሬ ማለዳውን ጨምሮ ሰሞኑን አዲስ አበባ እየገቡም ቆይተዋል።ጉባኤው “የአፍሪካ አኅጉርን የሥርዓተ ምግብ አቅም በመገንባት፤ የሰው ሃብት ልማት፣ የኢኮኖሚና ማኅበራዊ ልማትን ያፋጥናል” በሚል መሪ ሃሳብ ዛሬ እና ነገ የሚካሄድ ይሆናል።ኢትዮጵያ በሊቀመንበርነት የምትመራው የሁሉን አቀፍ የአፍሪካ የግብርና ዕድገት ፕሮግራም አፈጻጸምም ይቀርባል።ሪፖርቱንም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ያቀርቡታል ተብሎ ይጠበቃል። ይህም […]

በመካሄድ ላይ ባለው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ በኮቪድ-19 ምክንያት የተከሰቱ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችሉና በአፍሪካ ሰላምና መረጋጋትን የሚያሰፍኑ ውሳኔዎችን እንጠብቃለን ሲሉ የጉባኤው ተሳታፊዎች ገለጹ።

ተሳታፊዎቹ በዚህ ጉባኤ በአፍሪካ የተከሰቱ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችሉ ውሳኔዎች ይወሰናሉ ብለው እንደሚጠብቁ ለኢዜአ ተናግረዋል።የአፍሪካ ህብረት በጉባኤው ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ጉዳይ የወጣቶች ስራ ፈጠራን ማጠናከር ነው ያሉት ተሳታፊዎቹ ፥ ይህም ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮችን መፍታት ያስችላል ብለዋል።ውሳኔዎቹ አፍሪካ የሚያጋጥሟትን ችግሮች ተሻግራ ድል እንድታደርግ የሚያስችሉ ናቸው።በአፍሪካ በሴቶችና ህጻናት እንዲሁም በሌሎች ላይ ለሚከሰቱ ችግሮች መፍትሄ ለመስጠት መስራት […]

ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለው ለውጥ ለዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ መሠረት መሆኑን የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ ገለጹ፡፡

የኢፌዴሪ የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ በሳፋሪኮም የኬንያ ኃላፊ ሚካኤል ጆሴፍ ከተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ጋር ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸውም በቅርቡ በኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎት ለመስጠት እየተዘጋጀ የሚገኘው ሳፋሪኮም አባል የሆነበት የዓለም አቀፍ ጥምረት ለኢትዮጵያ እያከናወናቸው ባሉ እና ወደፊት በሚያከናውናቸው ሥራዎች ዙሪያ መክረዋል ፡፡ ዶክተር ፍጹም ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት እያካሄደችው ባለው ለውጥ የአገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያን […]

የአፍሪካ ሕብረት 40ኛው የስራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት ጉባኤ የሕብረቱ አባል ሀገራት ሚኒስትሮችና የአህጉሩ ልዩ ልዩ ተቋማት ሃላፊዎች በተገኙበት ዛሬ ተጀምሯል፡፡

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሃመት በጉባኤው መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር ፥ በአፍሪካ በየአቅጣጫው እያጋጠመ ያለውን የተለያየ ቅርፅ የሰላም እና ፀጥታ ችግር ለመፍታት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ሊቀመንበሩ ፥ የኮሮና ቫይረስ የፈጠረው ተፅዕኖ እና ለመቋቋም እየተደረገ ስላለው ጥረት፣ የአፍሪካ ህብረት የቀረጸው አጀንዳ 2063 የአፈጻጸም ሂደት፣ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና አተገባበር እንቅስቃሴ እና መሰል […]

ጀነራል ባጫ ደበሌ በመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ የመቆያ ጊዜያቸውን ለሸፈኑና በግዳጅ አፈፃፀማቸው ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የማዕረግ ዕድገት በሰጡበት ወቅት ሰራዊቱ ውስጣዊ አንድነቱን መጠበቅ እዳለበት አስገነዘቡ፡፡

የውስጥና የውጭ ፀረ ሰላም ሀይሎች ሰራዊታችንን በዘርና በሀይማኖት ለመከፋፈል በሚዲያ የሚያሰራጩትን አሉባልታዎች በመስማት የውስጣችንን አንድነት መሸርሸር የለብንም ሲሉ አሳስበዋል፡፡ማንኛውም ሰራዊት በመካከላችን ከተቀላቀለ ፕሮፌሽናል የኢትዮጵያ ሰራዊት ነው፤ የእኛ አላማ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ማሰከበርና ሰላሟን ማስጠበቅ ነው ብለዋል፡፡የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ ሀላፊ ሌ/ጀነራል ደስታ አብቼ በበኩላቸው÷ ሀገራችን አትበተንም በማለት የመሃንዲስ ክፍሉ ከፍተኛ አስተዋፆኦ አድርጓል ማለታቸውን ከመከላከያ ፌስቡክ ገጽ […]

Follow by Email
YouTube
YouTube
LinkedIn
LinkedIn
Share