Ethiopian News

የኢትዮጵያ መንግስት በኢትዮ-ሱዳን ድንበር የተፈጠረውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እየሰራ እነደሆነ አስታወቀ

አሁን ላይ በሁለቱ ሀገራት ድንበር ላይ ውጥረቱ ቢቀንስም ሙሉ በሙሉ እንዲፈታ መንግስት እየሰራ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል የተፈጠረው ግጭት የሁለቱን ሀገራት የቀደመ ታሪክ የማይመጥን ነው ተብሏል፡፡

የሚኒስቴሩ ቃለ አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የኢትዮጵያ መንግስት በኢትዮ-ሱዳን ድንበር የተፈጠረውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እየተሰራ እነደሆነም ተናግረዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴርና የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ደመቀ መኮንን ወደ ሱዳን ካርቱም አቅንተው በሰላማዊ መንገድ መፍታት በሚቻልበት መንገድ ላይ ተወያይተዋል ያሉት አምባሳደር ዲና፣ ሱዳን ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል ህግ በምታስከብርበት ወቅት ሱዳን የዲፕሎማሲ ድጋፏን አሳይታለች፤ ዜጎች ሲሰደዱም አስተናግዳለች፤ ይሄም እንደ በጎ ሊታይ የሚገባው ተግባር ነው ብለዋል፡፡

በቀጠናው አለመረጋጋት የሚያተርፉ አካላት ሁኔታዎች እንዲባባሱ እየሰሩ ነው የተባለ ሲሆን ሱዳናውያኑንም መሬቱ የናንተ ነው የሚል ቅስቀሳ በማድረግ በሀገራቱ መካከል ግጭት እንዲፈጠር ስለማድረጋቸው ተነስቷል፡፡ ዘገባው የዋልታ ነው፡፡

ታህሳስ 20,2013 ዓ.ም

በቀጣይ የሚከበሩ ሀይማኖታዊ በዓላትን ህብረተሰቡ ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ እንዲያከብር የጤና ሚኒስቴር አሳሰበ

ሚኒስቴሩ በዓላቱን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በመሆን በሰጠው መግለጫ ህዝብ በብዛት በሚሰበሰብባቸው በዓላት ወቅት ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል ብሏል፡፡

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤም በተለይም በአመታዊው የቅዱስ ገብርኤል የንግስ፣ የገና እና የጥምቀት በዓላት አከባበር ላይ፥ ምዕመኑ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ እንዲያከብር መልዕክት አስተላልፏል፡፡

ከዚህ ባለፈም ጉባኤው ወደቤተ እምነቶች የሚመጡ አማኞች የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል እንዲጠቀሙ እና የየቤተ እምነቱ መሪዎችና አስተዳዳሪዎች ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል እንዲያደርጉም አሳስቧል፡፡

በተጨማሪም ምዕመኑ በየትኛውም ሁኔታ አካላዊ ርቀትን በመጠበቅና ንክኪን በመቀነስ እንዲሁም ንጽህናን በመጠበቅ የቫይረሱን ስርጭትና ያለውን ተጋላጭነት እንዲቀንስም መልዕክት አስተላልፏል፡፡

እንዲሁም የኮሮና ቫይረስ ተጨባጭ የጤና ችግር መሆኑን በመረዳት ለአፍታም ቢሆን መዘናጋት አይገባምም ማለቱን ጠቅሶ ኤፍቢሲ ዘግቧል፡፡

ታህሳስ 16,2013 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ድምጽ መስጫ ቀን ግንቦት 28 እንዲሆን አሳውቀ

የምርጫ ቦርዱ በተጨማሪ የአዲስ አበባ ከተማ እና የድሬደዋ ከተማ መስተዳድር የድምጽ መስጫ ቀን ሰኔ 5 መሆኑን ገልጿል።

ዝርዝር የጊዜ ሰሌዳውን ይፋ ያደረገው ቦርዱ የምርጫ ጊዜ ሰሌዳው የትግራይ ክልልን አያካትትም ብሏል፡፡

የምርጫ ቢሮዎች መከፈት የክልል መስተዳድር አባላት ከፍተኛ ትብብር ስለሚያስፈልገው፤ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ይህንን ድጋፍ ለማድረግ ጊዜ ስለሚያስፈልገው እንዲሁም በክልሉ የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለምርጫ በሚስማማ መልኩ መመቻቸቱ ሲረጋገጥ በክልሉ የሚደረገው ምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ቦርዱ እንደሚያሳውቅም ምርጫ ቦርድ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጠቁሟል፡፡

ታህሳስ 16,2013 ዓ.ም

በትግራይ ክልል በዳንሻ፣ በተርካን፣ በሁመራ፣ በሸራሮ፣ ማይጸብሪና እና ማይካድራ በከፊል እንዲሁም በአላማጣ ሙሉ በሙሉ የቴሌኮም አገልግሎት ጀመረ

በአካባቢው በቴሌኮም መሰረተ ልማቶች ላይ ያጋጠሙ ጉዳቶችን በመጠገንና መልሶ በማቋቋም እንዲሁም አማራጭ የሃይል አቅርቦቶችን በመጠቀም የቴሌኮም አገልግሎት በከፊልና ሙሉ በሙሉ መጀመሩን ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል፡፡

በዚህም መሰረት በዳንሻ፣ በተርካን፣ በሁመራ፣ በሸራሮ፣ ማይጸብሪና እና ማይካድራ በከፊል እንዲሁም በአላማጣ ሙሉ በሙሉ የቴሌኮም አገልግሎት ማስጀመሩን ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል፡፡

በሌሎች አካባቢዎች የቴሌኮም አገልግሎት ለማስጀመር የተጎዱ የቴሌኮም መሰረተ ልማቶችን በመጠገን፣ መልሶ በማቋቋም ብሎም መደበኛ የኃይል አቅርቦትን ለማግኘት ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በጋራ እየተሰራ እንደሚገኝ አመላክቷል፡፡
ምንጭ፡ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ

ህዳር 23, 2013 ዓ.ም.

በአዲስ አበባ ከተማ የጎርጎርዮስ አደባባይ አካባቢ በፈነዳው ቦምብ ምንም የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ

ቦምቡ በቦሌ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው ጎርጎርዮስ አደባባይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኝ አንድ የቆሻሻ መጣያ ገንዳ ውስጥ ተጥሎ መገኘቱን ኮሚሽኑ ጠቅሷል፡፡

በዚህም ከአካባቢው ሰዎች በደረሰው ጥቆማ የፈንጅ አምካኝ ባለሙያዎች በማለዳ ወደ ስፍራው በማቅናት ለማምከን ባደረገው ሙከራ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ሊፈነዳ መቻሉን ነው ኮሚሽኑ ያስታወቀው፡፡

በዚህም አንድ ግለሰብ በፍንጣሪው ቀላል ጉዳት የደረሰበት ሲሆን ተጎጂው የህክምና እርዳታ በማግኘት ወደ ቤቱ ተመልሷል፡፡

በተመሳሳይ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ጉርድ ሾላ ቅዱስ ያሬድ ሆስፒታል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ለፖሊስ በደረሰ መረጃ መሰረት ባለሙያዎች ቦታው ድረስ በመገኘት ቦምቡን ማምከናቸውን ነው ኮሚሽኑ የገለጸው፡፡

ፖሊስ ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ባላቸው ግለሰቦችና አጠቃላይ የምርመራውን ውጤት እንደሚያሳውቅ አስታውቋል፡፡

ኮሚሽኑ ህብረተሰቡ ከፖሊስ ጋር የሚኖረውን የመረጃ ልውውጥ በማጠናከር አካባቢውን በንቃት እንዲጠብቅ ጥሪ ማቅረቡን የመዲናዋን ፖሊስ ኮሚሽን ጠቅሶ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዘግቧል፡፡

ህዳር 23, 2013 ዓ.ም.

የዋፋ ማርኬቲንግ እና ፕሮሞሽን ሰራተኞች የደም ልገሳ መርኀ ግብር አካሄዱ

መርኀ ግብሩን በይፋ ያስጀመሩት በሚንስትር ድኤታ ማእረግ የብልጽግና ፓርቲ የፓለቲካ ዘርፍ ም/ኋላፊ ክቡር አቶ ሙሳ መሀመድ “የህዝቡን እንባ ለማበስ ከሰራዊቱ ጎን በመሰለፍ ደም በመለገስ ላሳያችሁት ተነሳሽነት ከልብ አመሰግናለሁ” ሲሉ ምስጋናቸውን ለድርጅቱ ሰራተኞች ገልጸዋል፡፡
የዋፋ ማርኬቲንግ እና ፕሮሞሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ ፋንታዬ ጌታነህ በበኩላቸው ደግሞ የዋፋ ማርኬቲንግ እና ፕሮሞሽን ሰራተኞች ያደረጉት የደም ልገሳ ማድረግ ከሚገባን እጅግ ጥቂቱ ብቻ ነው ያሉ ሲሆን በክፎዎች የተፈጸመበትን ክፉ ደባ በድል ላጠናቀቀው የመከላከያ ሰራዎታችን ውለታውን ለመመለስ እንገደዳለን ብለዋል፡፡
ከደም ልገሳው በተጨማሪ የድርጅቱ ሰራተኞች ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ከወር ደሞዛቸው ግማሽ ያህሉን መስጠታቸው የሚታወስ ነው፡፡

ህዳር 22, 2013 ዓ.ም.

በአንድ ሳምንት ብቻ 42 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የተለያዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

ከህዳር 11 እስከ 17 2013 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ግምታዊ ዋጋቸው 42 ሚሊዮን 7 መቶ 49 ሺ በላይ የሚያወጡ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች ጥይት፣ አደንዛዥ ዕጽ፣ ቡና፣ ግመሎች እና የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በተለያዩ የጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች ተይዘዋል፡፡

ዕቃዎቹ ሊያዙ የቻሉት በጉምሩክ ሰራተኞች፣ በአካባቢው ህብረተሰብ ጥቆማ፣ በክልል ፖሊስ፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በአድማ በታኝና በመከላከያ አባላት የጋራ ጥረት መሆኑ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ከኮንትሮባንድ ዕቃዎች ማስተላለፍ ጋር ተያይዞ የተለያዩ አካላትና አሸከርካሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ ይገኛል፡፡

ህዳር 18, 2013 ዓ.ም.

ብሄራዊ የቴሌኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ፍቃድ እስከ ሚያዝያ ወር 2013 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል ተባለ

ብሄራዊ የቴሌኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ፍቃድ እስከ ሚያዝያ ወር 2013 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል ተባለ
የኢትዮጵያ ኮሙዩኒኬሽን ባለስልጣን ፈቃዶችን ለመስጠት የጨረታ መወዳደሪያ ሃሳብ መጠየቂያ ሰነድ ማውጣቱን ይፋ ያደረገ ሲሆን ውድድሩ ፍትሃዊ እንዲሆን የሚያስችለው ሂደት መገባደዱንም የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር እዮብ ተካልኝ ተናግረዋል፡፡
ጨረታው ለሶስት ወራት እንደሚቆይ የገለፁት ዶክተር እዮብ ከዚህ ቀደም ፍላጎት ያሳዩትን ጨምሮ በርካታ ዓለም አቀፍ ተቋማት እንዲሳተፉ ይደረጋል ነው ያሉት፡፡

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ባልቻ ሬባ በበኩላቸው የቴሌኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ፈቃዶችን ለመስጠት የሚሰራው ስራ በጥንቃቄ እየተካሄደ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ሰነዱም በባለስልጣኑ ድረገጽ እንደሚገኝ እና በቅርቡም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተደራሽ ህትመት እንደሚኖረውም ማስረዳተቸውንም የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዘገባ ያሳያል፡፡

ህዳር 18, 2013 ዓ.ም.

Premier Waves off undue intervention

Prime minister Abiy Ahmed (Phd) has called up on the international community to standby until the ‘government of Ethiopia submits its request for assistance to the community of nations’.

In a statement issued today the premier urged the international community to refrain from intervening in the internal affairs of the country and handle the matter as per rules of international law.

The statement also noted that the target of the law enforcement operations; TPLF has been wreaking havoc and working to destabilize the nation for the past three years.

Accordingly, the premier stressed the need to secure law and order stating “as a sovereign state Ethiopia has every right to uphold and enforce its laws within its territory. And that is exactly what we are doing”.

He then expressed his appreciation all concerns and advices provided by friends of the nation while rejecting any interference in the county’s internal affair as well as urging the international community to respect the fundamental principles of non-intervention under international law.

Nov 25th, 2020