Ethiopian News

በሀገሪቷ ውስጥ የሚካሄዱ ሁነቶች ከፕሮቶኮል አንፃር ብዙ ሊሰራባቸው እንደሚገባ ተገለፀ፡፡

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከዋፋ ማርኬቲንግና ፕሮሞሽን የማኔጅመንት አባላት ጋር በተቋሙ አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴና በቀጣይ ሊተኮርባቸው በሚገቡ ተግባራት ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡
በሀገሪቱ ውስጥ የሚካሄዱ ሁነቶች ወጪ ቆጣቢ፣ ደረጃቸውን የጠበቁና የታለመላቸውን ዓላማ የሚያሳኩ ሆነው ይዘጋጁ ዘንድ ወጥነት ያለውና ዓለም አቀፍ የሁነት ዝግጅት ፕሮቶኮሎችን የተከተለ አሰራር በመዘርጋትና አስፈላጊውን ስልጠና በመስጠት ረገድ ዋፋ ማርኬቲንግና ፕሮሞሽን ከፍተኛ ኃላፊነት እንዳለበት ፕሬዚዳንቷ ገልፀዋል፡፡
የዋፋ ማርኬቲንግና ፕሮሞሽን ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ፋንታዬ ጌታነህ በበኩላቸው ተቋሙ የሀገሪቱን መልካም ገፅታ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ እያደረገ ያለውን ጥረት ይበልጥ ለማጠናከር እየሰራ መሆኑን አስታውሰው የሀገሪቱን የሁነት ኢንዱስትሪ አሁን ካለበት ደረጃ ከፍ ለማድረግ የበኩሉን ድርሻ በመወጣት ላይ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡

ሐምሌ 19, 2013 ዓ.ም

ከድሬድዋ ወደ ጅግጅጋ ሲጓዝ የነበረ ET-AMl መለስተኛ አውሮፕላን በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ኮምቦልቻ ወረዳ ዛሬ ወደቀ፡፡

በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩ ሰዎች በህይወት መትረፋቸውም ታውቋል፡፡

አውሮፕላኑ ዛሬ ከቀኑ 11:30 አካባቢ በኮምቦልቻ ወረዳ ቄረንሳ ጋረአሮ በተባለ ቦታ መውደቁን የወረዳው ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብዲ ቡሽራ ተናግረዋል፡፡

ከተሳፋሪዎች መካከል በአንደኛው ተጓዝ ላይ መጠነኛ ጉዳት የደረሰበት በመሆኑ ወደ ድሬደዋ ለህክምና መላኩንም መግለጻቸውን ባልደረባችን ተሾመ ሀይሉ የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ ሬዲዮን ጠቅሶ ዝግቧል።  (ኤፍ ቢ ሲ)

ሐምሌ 21, 2013 ዓ.ም

ከታላቁ የህዳሴ ግድብ አሁንም ዓይናችንን ለአፍታ አንነቅልም – ሜጄር ጀኔራል ይልማ መርዳሳ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ከታላቁ የህዳሴ ግድብ ዓይናችንን ለአፍታ ሳንነቅል ደህንነቱን እየጠበቅን እንገኛለን ሲሉ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሜጄር ጀኔራል ይልማ መርዳሳ ተናገሩ።
የኢፌዴሪ አየር ኃይል መንግስት በሚሰጠን ትእዛዝ መሰረት ሀገር ለማፍረስ በሚጥር የትኛውም ኃይል ላይ በሚፈለገው ቦታና ጊዜ ጥቃት ለመፈጸም ዝግጁ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።
ሜጀር ጄኔራል ይልማ መርዳሳ እንደተናገሩት፥ ከታላቁ የህዳሴ ግድብ ጋር ተያይዞ የተከሰቱ የውጭ ጫናዎችና የውስጥ ትንኮሳዎች የኢትዮጵያ ወቅታዊ ፈተናዎች ሆነው ቆይተዋል።
“ኢትዮጵያ በቀጣናው ያላትን ተጽዕኖ የማይፈልጉ የውጭ ኃይሎች ከውስጥ ባንዳዎች ጋር ተቀናጅተው የተለያዩ ጫናዎችን ሲያደርጉ ቆይተዋል” ነው ያሉት።
የእነዚህ ኃይሎች ዋነኛ ዓላማ የኢትዮጵያ ህዝብ በራሱ ወጪ እየገነባ ያለው የህዳሴ ግድብ በከንቱ ማስቀረት መሆኑንም አስረድተዋል።
ከዚህ አኳያ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት መጠናቀቁ ለኢትዮጵያውያን ልዩ ትርጉም እንዳለው ጠቅሰው፥ ድሉ መንግስትና ህዝብ አንድ ሆነውና ተናበው ከሰሩ ምን መፍጠር እንደሚችሉ አመላካች መሆኑን አብራርተዋል።
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛው ዙር ውሃ ሙሌት በስኬት መጠናቀቅ በተለይ ሌት ተቀን ግድቡን እየጠበቀ ላለው የኢፌዴሪ አየር ኃይል ልዩ የደስታ ስሜት እንደፈጠረም ተናግረዋል።
አየር ኃይላችን በግድቡ ላይ ሊጋረጡ የሚችሉ “ውጫዊ ስጋቶችን ጠንቅቆ ይገነዘባል” ያሉት ሜጄር ጀኔራል ይልማ።
በዚህም “ዓይናችንን ከግድቡ ላይ ለአፍታ ሳንነቅል ደህንነቱን የመጠበቅ ተልዕኳችንን እንወጣለን” ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
መንግስት በትግራይ ክልል ሃገር ለማፍረስ ሲንቀሳቀስ በነበረው አሸባሪ ቡድን ላይ በወሰደው የህግ ማስከበር እርምጃ የኢፌዴሪ አየር ኃይል አበርክቶ ጉልህ እንደነበርም ነው ሜጄር ጀኔራል ይልማ መርዳሳ ያስታወሱት።
ለሃገርና ህዝብ ጥቅም ዴንታ የሌለው ኃይል “ሃገር ለማፍረስ በተደጋጋሚ ሞክሮ አልተሳካለትም፤ አሁንም በሚችለው አቅም ሙከራ እያደረገ ይገኛል” ብለዋል።
በመሆኑም አየር ኃይሉ ከመንግስት በሚሰጠው ትእዛዝ መሰረት አገር ለማፍረስ የሚጥሩ ኃይሎች ላይ በየትኛውም ቦታ ጥቃት ለመፈጸም ከመቼውም ጊዜ በላይ ዝግጁ መሆኑንም ገልጸዋል።
የኢፌዴሪ አየር ኃይል የትኛውንም የህልውና አደጋ ለመቀልበስ ከመቼውም ጊዜ በላቀ ቁመና እና ስነ-ልቦናዊ ዝግጅት ላይ እንደሚገኝም ሜጄር ጀኔራል ይልማ ተናግረዋል።
የመከላከያ ሰራዊት ከየትኛውም የፖለቲካ ወገንተኝነት ነጻ በሆነ መልኩ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እንዲጠብቅ ተደርጎ መደራጀቱን የገለጹት ዋና አዛዡ፥ የኢፌዴሪ አየር ኃይል ከዚህ አኳያ የሰው ኃይል ግንባታን መሰረት ያደረገ ውጤታማ የሪፎርም ስራዎች መከናወኑን ተናግረዋል።
በለውጥ ስራዎች አማካኝነትም ወቅቱን የሚመጥን ብቁ የሰው ኃይል ማፍራት እንደተቻለ ጠቅሰው፥ የለውጥ ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።
ኢትዮጵያውያን በየትኛውም ግዳጅ ላይ ለሚገኝ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እያደረጉት ያለውን ድጋፍ አድንቀው፥ ይህ ተግባር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሜጄር ጀኔራል ይልማ ጥሪ አቅርበዋል።

ሐምሌ 17, 2013 ዓ.ም

ዓም የሁለተኛውን አመት የህዳሴ ግድብ ሙሌት ተገባዶ ውሃው በግድቡ አናት ላይ መፈሰስ ጀመረ

ዛሬ ሐምሌ 12 ቀን 2013 ዓም የሁለተኛውን አመት የህዳሴ ግድብ ሙሌት ተገባዶ ውሃው በግድቡ አናት ላይ መፈሰስ መጀመሩን የውሃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።

ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ በትዊተር ገጻቸው ላይ ÷ ውሃው በግድቡ አናት ላይ መፍሰስ ጀምሯል ብለዋል። (ኤፍ ቢ ሲ) 

ሐምሌ 12, 2013 ዓ.ም

ወንጀል ሊያጋጥሙ የሚችሉ ጉዳዮች ላይ ማንነት እንዲያረጋግጡ የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳሰበ፡፡

በ አዲሰ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች ማንነታቸውን ሰውረው መኖሪያ ቤቶችንና መኝታ ቤቶችን በመከራየት ወንጀል ለመፈፀም አቅደው የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች ስለመኖራቸው የፖሊስ የምርመራ መዛግብት ያስረዳሉ፡፡

የከተማዋን ሠላም በዘላቂነት ማስቀጠል የተቻለው በፀጥታ አካላት ቁርጠኝነት እና በህብረተሰቡ የነቃ ወተሳትፎ መሆኑን የገለፀው ፖሊሰ አሁንም ይህንን ሰላም አሰተማማኝ አድርጎ ማቆየት እንዲቻል ከመቼውም ጊዜ በላይ ለፀጥታ ስራ ልዩ ትኩረት መስጠት የሚያስፈልግበት ውቅት ላይ እንገኛለን ብሏል፡፡

የአ/አበባ ፖሊስ ከህብረተሰቡና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት እየሰራ መሆኑን ገልፆ ወንጀል ፈፃሚዎችና ሌሎች የፀጥታ ችግሮችን ለመፍጠር የሚንቀሳቀሱ አካላት ምቹ ሁኔታ እንዳይኖራቸው ማድረግ ተገቢ መሆኑን አስገንዝቧል፡፡

ይህንን ለማሳካት በዋናነት የመኖሪያ ቤት የሚያከራዩ ግለሰቦች ፤የመኝታአገልግሎት በሚሰጡ ሆቴሎች፣ ፔንሰሊዮኖችና ተመሣሣይ አገልግሎት የሚሰጡ የንግድ ቤቶች ማንነታቸው በግልፅ ላልታወቁ ሰዎች ቤት እንዳያከራዩ እንዲሁም በሚያከራዩበት ወቅት የተከራዩን ማንነት የሚገልፁ የነዋሪነት መታወቂያና ሌሎች ሰነዶችን በሚገባ አረጋግጠው በመመዝገብ ይህንንም በየአቅራቢያቸው ለሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ማሳወቅ እንደሚጠበቅባቸው የአዲሰ አበባ ፖሊስ አሳስቧል፡፡

የጥፋት ተልኮ ተቀብለው የሚንቀሳቀሱና ለአካባቢያቸው እንግዳ የሆኑ ፀጉረ ለውጦች ሲያጋጥሙም በአቅራቢያቸው ለሚገኙ የፀጥታ አካለት ጥቆማና መረጃ እንዲሰጡ ፖሊስ ጠይቋል፡፡ (ኤፍ ቢ ሲ )

ሐምሌ 11, 2013 ዓ.ም

በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ልዑክ ወደ ኬንያ አቅንቷል።

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጸሐፊ የሚመራ ልዑክ ከኬኒያው አቻው ጋር በሁለትዮሽና በቀጠናው ሠላም ዙሪያ የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ዛሬ ማምሻውን ወደ ኬንያ አቅንቷል።

የተቋሙ ዋና ጸሐፊ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ልዑኩ በናይሮቢ በሚኖረው የአራት ቀናት ቆይታ ከኬንያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በሁለትዮሽና በቀጠናው ሠላም ዙሪያ ውይይቶች እና የልምድ ልውውጦች ያደርጋል

በተለይም ልዑኩ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ በቅርቡ በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት የኬንያ መንግስት ከኢትዮጵያ መንግስት ጎን በመቆሙ ላሳዩት አቋም ምስጋናም እንደሚቀርብም አስታውቀዋል።

በሌላ በኩል ከኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አባላት እና የሃይማኖት አባቶች ጋር ውይይት እንደሚደረግና በኬንያ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከሀገር ውጭ ከአሜሪካ በመቀጠል ሁለተኛውን ቅርንጫፍ ለማቋቋም እንደሚመክር ነው ዋናዉ ጸሐፊው የገለጹት። (ኤፍ )

ሐምሌ 10, 2013 ዓ.ም

Follow by Email
YouTube
YouTube
LinkedIn
LinkedIn
Share