Auto Draft

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ስር የሚገኘው ብሔራዊ የመረጃና ደህንነት ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ከሪፐብሊካን ጋርድ የተመለመሉ በቪአይፒ እና በቁልፍ መሰረተ ልማት ጥበቃ የሰለጠኑ መኮንኖችን አስመርቋል፡፡
የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ተመስገን ጥሩነህ በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የሪፐብሊካን ጋርድ አባላት ትልቅ ሃላፊነትና እምነት የተጣለባቸው ሲሆን፤ የሀገርን ብሔራዊ ደህንነት በማረጋገጥ ረገድም ከፍተኛ ሚና ሲያበረክቱ እንደነበር ገልጸዋል፡፡
በተለይ ከሀገራዊ ለውጡ ጋር ተያይዞ ያጋጠሙ ፈተናዎችን በከፍተኛ ወኔና ትዕግስት በመፍታት ያበረከቱት አስተዋጽኦ አስቸጋሪ ጊዜዎችን ለማለፍ እንዳስቻለ ያስታወሱት አቶ ተመስገን፤በቀጣይ ተልዕኳቸውን በብቃትና ጥብቅ በሆነ የስራ ዲሲፒሊኒ ለመወጣት የሚስችላቸውን ስልጠና ከዩኒቪርሲቲ ኮሌጁ መቅሰማቸውን አመልክተዋል፡

ጳጉሜ 3, 2013 ዓ.ም

Please follow and like us:
Follow by Email
YouTube
YouTube
LinkedIn
LinkedIn
Share