ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ተገኝተው ለአቅመ ደካሞች እና አረጋውያን ማዕድ አጋርተዋል፡፡

ወረዳው በርካታ ችግሮች ያሉበት ስለመሆኑ ግንዛቤው አለኝ ያሉት ፕሬዝዳንቷ የዜጎችን ኑሮ በዘላቂነት ለማሻሻል ስራዎች እየተሰሩ ስለመሆኑ አንስተዋል፡፡
በተለይ ሴቶች በተለያዩ የስራ ዘርፎች ላይ ተሰማርተው ኑሯቸውን በዘላቂነት እንዲያሻሽሉ የሚያስችላቸውን መንገድ ለመፍጠር ስራዎች መጀመራቸው ገልጸዋል፡፡
በአካባቢው ወጣቶች ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን የሚያደርጉበት ቦታ ለማመቻቸትም ጥረት እየተደረገ ነው ማለታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
መጪው ቀን የበዓል በመሆኑ ለአቅመ ደካሞች ድጋፍ ያደረጉት ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ÷በመልካምነት የሚሰሩ ስራዎች በዘላቂነት የዜጎችን ህይወት የሚያሻሽሉ እና መሬት ወርደው የሚታዩ ሊሆኑ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡(ኤፍ ቢ ሲ)

ጳጉሜ 03, 2013 ዓ.ም

Please follow and like us:
Follow by Email
YouTube
YouTube
LinkedIn
LinkedIn
Share