ጸጥታው ምክር ቤት የተያዙ አቋሞች ከሞላ ጎደል የኢትዮጵያን እውነታ የተገነዘቡ መሆናቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምበሳደር ዲና ሙፍቲ አስታወቁ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምበሳደር ዲና ሙፍቲ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፥ በትናንትናው እለት በጸጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያን አጀንዳ ተመልክቶ በአባል አገራቱ የተያዘው አቋም ከሞላ ጎደል ያለውን እውነታ የተገነዘበ ነበር፡፡
የተለያዩ አቋሞች ተንጸባርቀዋል ለማለት አያስችልም ያሉት አምባሳደሩ፥ የኢትዮጵያን አቋም ያራመዱት ሩሲያ፣ ቻይና፣ ህንድና ኬንያ በተለየ ሁኔታ ድጋፋቸውን አሳይተዋል፡፡
በጥቅሉ ከአንድ ሀገር በስተቀር የተቀሩት ሀገራት ከሞላ ጎደል የቀረቡበት ሁኔታ ጥሩ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
አሜሪካም በጸጥተው ምክር ቤት የነበራት አቋም አሸባሪው ህወሓትን ማውገዝ የጀመረችበት ሁኔታ መኖሩን የገለጹት አምበሳደሩ፥ የተነሱ ሀሳቦች በበጎው የሚታዩ ናቸው ብለዋል፡፡
ጠንከር ብለው የኢትጵያን አቋም ላራመዱና ለደገፉ ሀገራት እና የኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ በመሆኑ በአፍሪካ ማዕቀፍ እንዲፈታ ድጋፍ ላደረጉ ሀገሮች መስጋናችን እናቀርባለን ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ጉዳይ ኢትዮጵያዊ መር ሆኖ አፍሪካዊያን ድጋፍ እንዲያደርጉና ሌሎች ወዳጆች ደግሞ ከውጭ ሆነው ይደግፉ የሚለውን አቋም ሁሉም የተቀበሉት ይመስላል ብለዋል፡፡(ኤፍ ቢ ሲ)

ነሐሴ 21, 2013 ዓ.ም

Please follow and like us:
Follow by Email
YouTube
YouTube
LinkedIn
LinkedIn
Share