ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አለም አቀፉ ማህበረሰብ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳዮች ላይ አግባብነት የሌለው ጣልቃ ገብነትን ከመተግበር እንዲቆጠብ ጥሪ አቀረቡ

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) አለም አቀፉ ማህበረሰብ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳዮች ላይ አግባብነት የሌለው ጣልቃ ገብነትን ከመተግበር እንዲቆጠብ ጥሪ አቀረቡ፡፡

ጠቅላይ ሚንስትሩ ዛሬ በይፋዊ የማህበራዊ ገጻቻቸው ላይ ባሰፈሩት መግለጫ አለምአቀፉ ማህበረሰብ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ከሚገኘው የህግ ማስከበር እንቅስቃሴ ጋር ተያይዞ እያሳየ የሚገኘውን ትኩረት በማመስገን ከአለም አቀፍ ህግጋት ውጭ የሚደረጉ የትኛውም የጣልቃ ገብነት እንቅስቃሴዎች ግን ተቀባይነት የላቸውም ብለዋል፡፡

የህውሀት ቡድን በሀገሪቱ ላለፉት ሶስት አመታት የተለያዩ ህገ ወጥ እንቅስቃሴዎችን ሲያከናውን መቆየቱን ያስታወሱት ጠቅላይ ሚንስትሩ ኢትዮጵያ እንደ ሉአላዊት ሀገር የሀገሪቱን ህጎች በሀገሪቱ ውስጥ የማስከበር መብት አላትም ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ የተፈጠረውን ሁኔታ በሀገሪቱ ህጎች እና አለምአቀፍ ግዴታዎች መሰረት የመፍታት ሙሉ አቅም አላት ያሉት ጠቅላይ ሚንስትር አብይ ከዚህ አንጻር አለም አቀፉ ማህበረሰብ ማንኛውንም ጣልቃ ገብነት ከማድረጉ በፊት ከኢትዮጵያ መንግስት የእገዛ ጥሪ እስኪደርሰው ድረስ ሊጠባበቅ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡

ህዳር 16, 2013 ዓ.ም.

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Follow by Email
YouTube
YouTube
LinkedIn
LinkedIn
Share