የውስጥና የውጭ ፀረ ሰላም ሀይሎች ሰራዊታችንን በዘርና በሀይማኖት ለመከፋፈል በሚዲያ የሚያሰራጩትን አሉባልታዎች በመስማት የውስጣችንን አንድነት መሸርሸር የለብንም ሲሉ አሳስበዋል፡፡
ማንኛውም ሰራዊት በመካከላችን ከተቀላቀለ ፕሮፌሽናል የኢትዮጵያ ሰራዊት ነው፤ የእኛ አላማ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ማሰከበርና ሰላሟን ማስጠበቅ ነው ብለዋል፡፡
የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ ሀላፊ ሌ/ጀነራል ደስታ አብቼ በበኩላቸው÷ ሀገራችን አትበተንም በማለት የመሃንዲስ ክፍሉ ከፍተኛ አስተዋፆኦ አድርጓል ማለታቸውን ከመከላከያ ፌስቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የማዕረግ እድገት ያገኙ የሰራዊት አባላት በበኩላቸው÷ እንደ ሀገር ከፍተኛ ግዳጅ ፈፅመው የማዕረግ እድገት በማግኘታቸው እንደተደሰቱና በቀጣይ ለሚሰጠው ማንኛውም ግዳጅ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡(ኤፍ ቢ ሲ)