ዶክተር ቴዎድሮስ ድጋሜ እንዳይሾሙ!

የኤች.አይ.ቪ ጤና እንክብካቤ ፋውንዴሽን (ኤኤችኤፍ) ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባል ሀገራት ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ለሁለተኛ ጊዜ የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ሆነው እንዳይሾሙ ሲል ጥሪ አቀረበ፡፡ተቋሙ ጥሪውን ያቀረበው በቅርቡ በገለልተኛ አካል የድርጅቱ ኦዲት ግኝቱ ይፋ መደረጉን ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡በኦዲት ግኝቱ የዓለም ጤና ድርጅት በህገ ወጥ መልኩ 332 ነጥብ 79 ሚሊየን ዶላር ስምምነት መድረሱ ተነግሯል፡፡በተጨማሪም ዝቅተኛ ብቃት ላለው አማካሪ ድርጅት የድርጅቱን የጨረታ አሰራር ባልተከተለ መልኩ የ2 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ውል መስጠቱም ነው የተገለጸው፡፡የኦዲት ግኝቶቹ በድርጅቱ ውስጥ እየተከናወኑ ያሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮች እና አሰራሮቹም ግልፅነት የጎደላቸው እንደሆኑ ማሳያ ነው ተብሏል፡፡እንዲሁም በድርጅቱ ሙስናና ብልሹ አሰራር የተንሰራፋ ሲሆን ለክትባት ለመድሐኒት ግዢ የሚውለውን ገንዘብ በአግባባቡ ጥቅም ላይ እንዳይውል ተደርጓል ነው የተባለው፡፡በዓለም አቀፉ ገለልተኛ የፋይናንስ ተቋም የቀረበው ሪፖርቱ በዓለም ጤና ድርጅት ውስጥ የስነ ምግባር ጉድለትን ጨምሮ፤ማጭበርበር፣ ጾታዊ ጥቃት እንዲሁም ብልሹ አሰራር መንሰራፋቱን የቢዝነስ ዋዬር ዘገባ ያመላክታል፡፡ደብዳቤውን ለተመድ ያስገባው ኤኤችኤፍ የተሰኘው ተቋም በዓለም ላይ ትልቁ የኤች.አይ.ቪ /ኤድስ እንክብካቤ ፋውንዴሽን ተቋም (ኤፍቢሲ)

ሰኔ 24, 2013 ዓ.ም

Please follow and like us:
Follow by Email
YouTube
YouTube
LinkedIn
LinkedIn
Share