ባንኩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ፥ ይህ ዓለም አቀፍ የልማት ድጋፍ በኢትዮጵያ ግጭት በነበረባቸው አካባቢዎች የተጎዱ ሰዎችን መልሶ ለማቋቋም እና የወደሙ መሰረተ ልማቶችን መልሶ ለመገንባት እንደሚውል አስታውቋል።
በተለይም ድጋፉ የመሰረታዊ አገልግሎት አቅርቦትን ለማሻሸል እና ለዓየር ንብረት ለውጥ የማይበገር መሰረተ ልማት ለመገንባት እንደሚውል በመጠቆም፥ በግጭት የተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎችን እንደሚያስቀድም ነው ባንኩ ያመለከተው።
በዚህም መሰረት አፋር፣ አማራ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ኦሮሚያ እና ትግራይ ክልሎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑም አስታውቋል።
ውጤታማ እና ፈጣን ምላሽ ለመስጠትም በማሰብ የገንዘብ ድጋፉ በፌደራል መንግስት፣ በክልል መንግስታት እና በአካባቢዎቹ በሚንቀሳቀሱ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች በኩል እንደሚቀርብም ገልጿል። (ኤፍ ቢ ሲ)