የእስራኤል መንግስት በኢትዮጵያ የተከሰተውን የበረሃ አንበጣ ለመከላከል ለኬሚካል መርጫ የሚሆኑ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በመስጠት እንዲሁም የባለሙያ ግብረ ኃይል በመላክ ላደረገው ድጋፍ አቶ ደመቀ ምስጋና አቅርበዋል

የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋቢ አሽክናዚ ጋር በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ የስልክ ውይይት አድርገዋል፡፡ አቶ ደመቀ መንግስት በትግራይ ክልል እያካሄደ ስለሚገኘው የህግ ማስከበር ዘመቻ ለጋቢ አሽክናዚ ገለጻ አድርገውላቸዋል፡፡   በተጨማሪም የእስራኤል መንግስት በኢትዮጵያ የተከሰተውን የበረሃ አንበጣ ለመከላከል ለኬሚካል መርጫ የሚሆኑ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በመስጠት እንዲሁም የባለሙያ ግብረ ኃይል በመላክ ላደረገው ድጋፍ አቶ ደመቀ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋቢ አሽክናዚ በበኩላቸው የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በቅርብ እየተከታተሉት እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡ የታላቁ የህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድርም ወደ ውጤት እንደሚደርስ እምነታቸው መሆኑንም ጠቅሰዋል። (ኤፍ. ቢ.ሲ)

ህዳር 3, 2013 ዓ.ም.

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Follow by Email
YouTube
YouTube
LinkedIn
LinkedIn
Share