የእርሻ ወቅት እስኪጠናቀቅ ድረስ የሚቆይ ያለቅድመ ሁኔታ የሚተገበር የተኩስ አቁም በትግራይ!

የትግራይ ክልል ጊዜዬዊ አስተዳድር በጠየቀው መሠረት ገበሬው ተረጋግቶ የእርሻ ሥራውን እንዲከውን፣ የርዳታ ሥራው ከወታደራዊ እንቅቃሴ ነጻ ሆኖ እንዲሠራጭ፣ ሰላምን የሚመርጡ የሕወሐት ርዝራዥ አካላት ወደ ሰላም መንገድ እንዲመጡ፤ ሳያውቁ ርዝራዡን የጥፋት ኃይል የተከተሉ እንደገና ለማሰብና ወደ ሰላማዊ መንገድ ለመምጣት ዕድል እንዲያገኙ ለማስቻል፣ ይህ የእርሻ ወቅት እስኪጠናቀቅ ድረስ የሚቆይ ያለቅድመ ሁኔታ በሰብአዊነት ላይ የተመሠረተ በተናጠል የተኩስ አቁም ከዛሬ ከሰኔ 21 ቀን 2013 ጀምሮ መንግሥት አውጀዋል፡፡
ሁሉም የፌዴራልና የክልል ሲቪልና ወታደራዊ ተቋማት፣ ከመንግሥት በሚሰጣቸው ዝርዝር አፈጻጸም መሠረት ይሄን የተኩስ አቁም እንዲያከብሩና እንዲያስከብሩ ታዝዘዋል፡፡ ይሄን መልካም ዕድል ለክፉ የሚጠቀሙ ወገኖች ካጋጠሙ ግን አስፈላጊው ሕግን የማስከበር ተግባር እንደ አግባቡ የሚከናወን ይሆናል፡፡ ሲል የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡

Please follow and like us:
Follow by Email
YouTube
YouTube
LinkedIn
LinkedIn
Share