የኢትዮ- ፈረንሳይ የቢዝነስ ፎረም ተሳትፎ ግብዣ

ድርጅታችን ዋፋ ማርኬቲንግና ፕሮሞሽን ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ከሚመለከታቸው የሀገር ውስጥና የውጭ ተቋማት ጋር በመተባበር በፈረንሳይ ፓሪስ ከተማ እ.ኤ.አ. ከ አፕሪል 4-8 2022 ሊያዘጋጅ ታቅዶ የነበረው የንግድ፣ ኢንቨስትመንትና ቱሪዝም ፎረም በተለያየ ምክንያት ወደ ሜይ 23 ቀን 2022
( ግንቦት 15 ቀን 2014 ዓ.ም) መሸጋገሩን በአክብሮት እንገልጸለን፡፡
የፎረሙ ዋነኛ አላማ ከፈረንሳይ ጋር የዲፕሎማቲክ ግንኙነት የተጀመረበትን 125 ኛ ዓመት በማስመልከት የሁለቱን ሀገራት የንግድ ግንኙነት ለማጠናከር፣ ሀገራችን በተለያዩ የኢንቨስትመንት ና የቢዝነስ ዘርፎች በተለይም፣በአግሮ ፕሮሰሲንግ፣ በማኑፋክቸሪንግ ፣ በማዕድንና ኢነርጂ፣ በኮንስትራክሽን ፣ እንዲሁም፣ ሆቴልና ቱሪዝም ያሏትን አማራጮች በማስተዋወቅ ከፈረንሳይ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ፣ የውጭ ንግድ ምርቶቻችንን ለማስተዋወቅ፣ የቱሪስቶችን ፍሰት ለመጨመር እንዲሁም የቴክኖሎጂና የልምድ ልውውጥ ለማድረግ የሚያስችሉ ሁኔታዎች መፍጠር ሲሆን፣ ለመሳተፍ ፍላጎት ያላችሁ ድርጅቶች እስከ ሚያዚያ 20 ቀን 2014 ዓ.ም. በስልክ ቁጥር 0938323232 እና 0115526875 በመደወል መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን ፡፡
ማሳሰቢያ፡- ያለን የተሳትፎ ቦታ ውስን በመሆኑ አስቀድመው ለሚመጡና መስፈርቱን ለሚያሟሉ ተሳታፊዎች ብቻ ቅድሚያ የምንሰጥ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

መጋቢት 22, 2014 ዓ.ም

Please follow and like us:
Follow by Email
YouTube
YouTube
LinkedIn
LinkedIn
Share