የውይይት መመሪያ ሰነዱ የፖለቲካ ፓርቲዎች እርስ በእርስ የሚያደርጉት ውይይት እንዴት መካሄድ እንዳለበት የሚወስን መሆኑ ተመላክቷል፡፡
ሰነዱ በፓርቲዎች ከፀደቀበት ጊዜ ጀምሮ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚያደርጉት ውይይት እስከሚጠናቀቅበት ድረስ የጸና እንደሚሆን ነው የተገለጸው፡፡
አሁን ላይም በኢትዮጵያ ለግጭት ምክንያት ሆነዋል የሚባሉ ጉዳዮችንም ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች አጀንዳዎችን በማቅረብ ውይይት እየተደረገ ነው፡፡ (ኤፍ ቢ ሲ)