የኢትዮጵያ መንግስት በኢትዮ-ሱዳን ድንበር የተፈጠረውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እየሰራ እነደሆነ አስታወቀ

አሁን ላይ በሁለቱ ሀገራት ድንበር ላይ ውጥረቱ ቢቀንስም ሙሉ በሙሉ እንዲፈታ መንግስት እየሰራ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል የተፈጠረው ግጭት የሁለቱን ሀገራት የቀደመ ታሪክ የማይመጥን ነው ተብሏል፡፡

የሚኒስቴሩ ቃለ አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የኢትዮጵያ መንግስት በኢትዮ-ሱዳን ድንበር የተፈጠረውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እየተሰራ እነደሆነም ተናግረዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴርና የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ደመቀ መኮንን ወደ ሱዳን ካርቱም አቅንተው በሰላማዊ መንገድ መፍታት በሚቻልበት መንገድ ላይ ተወያይተዋል ያሉት አምባሳደር ዲና፣ ሱዳን ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል ህግ በምታስከብርበት ወቅት ሱዳን የዲፕሎማሲ ድጋፏን አሳይታለች፤ ዜጎች ሲሰደዱም አስተናግዳለች፤ ይሄም እንደ በጎ ሊታይ የሚገባው ተግባር ነው ብለዋል፡፡

በቀጠናው አለመረጋጋት የሚያተርፉ አካላት ሁኔታዎች እንዲባባሱ እየሰሩ ነው የተባለ ሲሆን ሱዳናውያኑንም መሬቱ የናንተ ነው የሚል ቅስቀሳ በማድረግ በሀገራቱ መካከል ግጭት እንዲፈጠር ስለማድረጋቸው ተነስቷል፡፡ ዘገባው የዋልታ ነው፡፡

ታህሳስ 20,2013 ዓ.ም

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Follow by Email
YouTube
YouTube
LinkedIn
LinkedIn
Share