የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል የተናጥል የተኩስ አቁም ማድረጉን ሃገራትና ዓለም አቀፍ ተቋማት እውቅና እየሰጡት መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ ከዚህ ቀደም ጥያቄ ሲያቀርቡ የነበሩ አካላት እርምጃውን አድንቀዋል ብለዋል።

የአፍሪካ ህብረት፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፣ አሜሪካ፣ ቻይና፣ ስዊዲን፣ የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች እርምጃውን እውቅና ከሰጡ ቀዳሚ ሃገራት መካከል እንደሚገኙበት ጠቅሰዋል፡፡

እርምጃው የውጭ ጣልቃ ገብነትን ለማክሰም ማገዙንም አውስተዋል፡፡

አያይዘውም በመንግስት ከተጠቀሱ ምክንያቶች ባለፈ ከህዳሴው ግድብ ጋር በተያያዘም ኢትዮጵያ ቅድሚያ የምትሰጣቸው ጉዳዮች በመኖራቸው ውሳኔን ተላልፏልም ነው ያሉት፡፡ (ኤፍ ቢ ሲ)

ሰኔ 24, 2013 ዓ.ም

Please follow and like us:
Follow by Email
YouTube
YouTube
LinkedIn
LinkedIn
Share