የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ባለ ስድስት ነጥብ ረቂቅ ቻርተር ዝግጅት መደረጉን አስታወቀ

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የአስተዳደር መዋቅር ማስተካከል እና የክልሉ ኢኮኖሚ እንዲያንሰራራ ማድረግን የመሳሰሉ ጉዳዮችን ያከተተ ባለ ስድስት ነጥብ ረቂቅ ቻርተር ዝግጅት መደረጉን አስታወቀ፡፡

እንደ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዘገባ በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ ሕጋዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ በዛሬው እለት ውይይት ያካሄደው ጊዜያዊ አስተዳደሩ በክልሉ ሰላም ለማምጣት በሚደረጉ ጥረቶች ዙሪያ ምክክር አድርጓል፡፡

የጊዜያዊ አስተዳደሩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋን ጨምሮ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ህጋዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች በውይይቱ ላይ የተገኙ ሲሆን በጊዜያዊ አስተዳደሩ በቀጣይ ሊሰሩ በታሰቡ ሰላም የማስፈን እና ሌሎችም ጉዳዮች ዙሪያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሳትፎ ምን መምሰል አለበት የሚለው ላይም ሀሳብ ተነስቶ ውይይት ተደርጎበታል።

በክልሉ ሊሠሩ የታሰቡ ሥራዎች ዙሪያ ለተሳታፊዎቹ በተደረገው ገለጻም በቻርተሩ በተጨማሪ በትግራይ ክልል ሰላምንና ደህንነትን ማረጋገጥ፣ የህግ የበላይነትን እና ፍትህን ማስጠበቅ፣ በክልሉ ተቋረጠውን ማኅበራዊ አገልግሎት ማስቀጠል እና ፖለቲካ ፓርቲዎች በሀገራዊ ምርጫ በነፃነት እንዲወዳደሩ ማስቻልም ተዘርዝረዋል ተብሏል።

ህዳር 10, 2013 ዓ.ም.

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Follow by Email
YouTube
YouTube
LinkedIn
LinkedIn
Share