የተለያዩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች በክብርት ዶ/ር አበበች ጎበና ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ

የተለያዩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች በክብርት ዶ/ር አበበች ጎበና ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ፡፡

 የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል በኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ ለዘላለም የሚኖሩ የደግነት ተምሳሌት ውድ እናት ክብርት ዶክተር አበበች ጎበናን ማጣታችን አሳዛኝ ነው ብለዋል::

 የጤና ሚኒስትር ወይዘሮ ሊያ ታደሰ ከ40 በላይ አመታት ህፃናትን በፍቅር በመንከባከብ እና ለቁምነገር በማብቃት የሚታወቁትና የብዙዎች እናት የነበሩት ክብርት ዶክተር አበበች ጎበና ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው እጅግ ያሳዝናል ነው ያሉት።

 ክብርት ዶክተር አበበች ክቡር የሆነውን የሰውን ልጅ ከጎዳና እያነሱ አጥበው፣ አብልተው፣ አስተምረው በርካታ ልጆችን ለቁም ነገር ማብቃት የቻሉ ጀግና ሴት እንደነበሩ ያስታወሰው የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ለቤተሰቦቻቸው፣ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲሁም የእርሳቸውን እንክብካቤ ለሚሹ ሕጻናት መጽናናትን ተመኝቷል። (ኤፍ ቢ ሲ)

ሰኔ 28, 2013 ዓ.ም

Please follow and like us:
Follow by Email
YouTube
YouTube
LinkedIn
LinkedIn
Share