የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት ሕንጻ ተመረቀ፡፡ ዋፋ ማርኬቲንግና ፕሮሞሽን ሁነቱን በደማቅ ሁኔታ አስተባብሯል፡፡

ብልጽግና ፓርቲ ያስገነባው የዋና ጽሕፈት ቤት ሕንጻ የፓርቲው ፕሬዝዳንት ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ፣ የፓርቲው ምክትል ፕሬዝዳንቶች አቶ ደመቀ መኮንን እና አቶ አደም ፋራህ እንዲሁም ሌሎች በርካታ የፓርቲው እና የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት የምረቃ ሥነ ሥርዓቱ እየተካሄደ ይገኛል።
ይህንን ባለ 9 ወለል ሕንጻ ለመገንባት 895 ሚሊየን ብር ወጪ መደረጉ በመርሃ ግብሩ ተመላክቷል፡፡
በውስጡ መዝናኛ እና መሰብሰቢያ አዳራሽን ጨምሮ በርካታ ፋሲሊቲዎችን ያካተተ ሲሆን ከ 3ሺህ በላይ ሰራተኞችም በግንባታው ተሳትፈዋል።
በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ እንደተገለጸው ሕንጻው በ4 ሺህ700 ካሬ መሬት ላይ ያረፈ ነው፡፡
በመርሃግብሩ ንግግር ያደረጉት የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ያማረ ህንጻ መገንባት ብቻ ሳይሆን ያማረ አስተሳሰብን መፍጠ አስፈላጊ ነው ብለዋል። ያማረ ሕንጻ ገንብቶ ያማረች ሀገርና ያማረ አስተሳሰብን መፍጠር የቀጣይ የፓርቲውና የህዝብ ስራ መሆን እንዳለበትም ገልጸዋል፡፡
የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ በበኩላቸው ህንጻው ከአባላቱ በተደረገ መዋጮ እና ከደጋፊዎቹ በተገኘ ድጋፍ የተገነባ መሆኑን አንስተዋል።

መጋቢት 5,2014 ዓ.ም

Please follow and like us:
Follow by Email
YouTube
YouTube
LinkedIn
LinkedIn
Share