ብልጽግና ፓርቲ ያስገነባው የዋና ጽሕፈት ቤት ኮምፕሌክስ ዛሬ መጋቢት 5/2014 ዓ. ም ከደቂቃዎች በኋላ ከፍተኛ የፓርቲውና የመንግሥት አመራሮች በሚገኙበት ይመረቃል። ሕንጻው ዘመኑን የዋጁ ቴክኖሎጅዎችን የያዘና ሥነ ውበታዊነትንም የጠበቀ ነው። ከደቂቃዎች በኋላ የሚከናወነውን ይህንን ኹነት ዋፋ ማርኬቲንግና ፕሮሞሽን ከሃሳብ ማመንጨት ጀምሮ ሁሉን አቀፍ በሆነ መንገድ እያስተባበረው ይገኛል። ዋፋ ህንፃውን በልዩ ሁኔታ ከማስዋብ ጀምሮ ጠቅላላ የሎጂስቲክስ አቅርቦት በማሟላት ደረጃውን የጠበቀ ሁነት እየከወነ ይገኛል።