የሕወሐት አመራሮች በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን እንዲሰጡ እና ተጨማሪ ግፍ ከመፈጸም እንዲታቀቡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ማጣሪያ ጥሪ አቀረበ

የእሥር ማዘዣ የወጣባቸው የሕወሐት አመራሮች በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን እንዲሰጡ እና ተጨማሪ ግፍ ከመፈጸም እንዲታቀቡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ማጣሪያ ጥሪ አቀረበ፡፡
“የመጨረሻዎቹን እንጥፍጣፊ ዕድሎች መጠቀም እጅግ ከከፋው ዕጣ ፈንታ ያድናቸዋል” ያለው የመረጃ ማጣሪያው በቡድኑ የተፈጸሙት ወንጀሎች በኢትዮጵያም ሆነ አቀፍ ሕግ የሚያስጠይቁ ከባድ ወንጀሎች መሆናቸውንም አስታውሷል፡፡

የቡድኑ አመራሮች እንደ ማይካድራ ባሉ ሥፍራዎች ኃይሎቻቸው እና ታማኞዎቻቸው የፈጸሟቸው አሰቃቂ ድርጊቶች ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች በዚሁ ወንጀለኛ ቡድን ሲቀነባበሩ ከነበሩ ሕዝብ የማስጨረስ ሥራዎች ጋር የሚያያዝ ነውም ተብሏል፡፡

የመረጃ ማጣሪያው አክሎም የፌዴራል መንግሥት እንደዚህ ላሉት አስከፊ የወንጀል ድርጊቶች ተጠያቂ የሆኑትን ለፍርድ ለማቅረብ ቁርጠኝነቱን በድጋሚ ይገልጻል ብሏል፡፡

ህዳር 10, 2013 ዓ.ም.

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Follow by Email
YouTube
YouTube
LinkedIn
LinkedIn
Share