ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በትግራይ ክልል መልሶ ማቋቋም ስራ እንዲያግዝ የኢትዮጵያ መንግስት ጥሪ አቀረበ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን መንግስት የወሰደውን የተናጥል የተኩስ አቁም በተመለከተ ተቀማጭነታቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ አምባሳደሮች እና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ ገለጻ እያደረጉ ነው፡፡

በዚህ ወቅትም መንግስት ከስምንት ወራት በፊት ወደ ህግ ማስከበር ዘመቻ የገባባቸውን ዋና ዋና ምክንያቶች አብራርተዋል፡፡

የተካሄደው የህግ ማስከበር ዘመቻ በአጭር ጊዜ ውስጥ የተጠናቀቀና ግቡን የመታ እንደነበር ገልጸዋል፡፡

ከዘመቻው መጠናቀቅ በኋላም የክልሉን ጊዜያዊ አስተዳደር በማቋቋም ክልሉን መልሶ ወደ መገንባትና ወደ ማቋቋም መገባቱንም አስረድተዋል፡፡

ድጋፍ ለሚሹ ወገኖችን የዕለት ደራሽ እና ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ቢሆንም የሽብር ቡድኑ መሰናክል እየፈጠረ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

በሽብር ቡድኑ የወደሙ እንደ ባንክና ቴሌኮም ያሉ መሰረተ ልማቶችን በመጠገን ወደ ስራ ለማስገባት ጥረት መደረጉን አውስተው÷አሁንም ድረስ ቡድኑ መሰል መሰረተ ልማቶችን ኢላማያደረጉ ጥቃቶችን እንደሚፈጽም ተናግረዋል፡፡  (ኤፍ ቢ ሲ)

ሰኔ 25, 2013 ዓ.ም

Please follow and like us:
Follow by Email
YouTube
YouTube
LinkedIn
LinkedIn
Share