ዋፋ ማርኬቲንግ እና ፕሮሞሽን ከኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ከፈረንሳዮ ሜዴፍ ኩባንያ ጋር በመተባበር የንግድ ኢንቨስትመንት እና ቱሪዝም ፎረም ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ አጋጣሚ ነው ሲሉ በፈረንሳይ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሄኖክ ተፈራ ተናገሩ፡፡

ዋፋ ማርኬቲንግ እና ፕሮሞሽን ከኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ከፈረንሳዮ ሜዴፍ ኩባንያ ጋር በመተባበር በመጋቢት ወር መባቻ የሚያዘጋጀው የኢትዮ ፈረንሳይ የንግድ ኢንቨስትመንት እና ቱሪዝም ፎረም ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ አጋጣሚ ነው ሲሉ በፈረንሳይ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሄኖክ ተፈራ ተናገሩ፡፡
አምባሰደሩ ከዋፋ ማርኬቲንግ እና ፕሮሞሽን ጋር ባደረጉት ቆይታ ላይ እንዳነሱት ፎረሙ የሁለቱን ሀገራት ዘርፈ ብዙ ግንኙነቶች ከማጠናከር አንጻር ከፍተኛ አዎንታዊ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ገልጸዋል፡፡
በተለይም በምጣኔ ሀብት እና ኢንቨስትመንት ዘርፍ ትልቅ ድጋፍ የሚያደርግ ነው ብለዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም የኢትዮጵያን እምቅ ጉልበት ለፈንሳይ ባለሀብቶች ለማሳየትም ትልቅ አንደሆነም አንስተዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም አምባሳደሩ ፎረሙን ላስባበሩት ድርጅቶች በተለይም ለዋፋ ማርኬቲንግ እና ፕሮሞሽን ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
ከመጋቢት 26 እስከ 28 2014 አ.ም በፈረንሳይ ፓሪስ የሚካሄደው ፎረሙ የተለያዮ የኢትጲያና የፈረንሳይ ባለሀብቶች እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ይገኙበታል፡፡

መጋቢት 8,2014 ዓ.ም

Please follow and like us:
Follow by Email
YouTube
YouTube
LinkedIn
LinkedIn
Share