ዋፋ ማርኬቲንግና ፕሮሞሽን ፣”ሀገሬን እገነባለሁ፣ ኃላፊነቴንም እውጣለሁኝ”በሚል ገዥ ሀሳብ የተሰናዳውን የወጣቶች ለሰላም ሀገር አቀፍ ንቅናቄ የማጠቃለያ መረሀ-ግብር በማስተባበር ላይ ይገኛል::

የዛሬው፣ የውይይት መድረክ ልዩ ልዩ የወጣት አደረጃጀቶች በየክልሎቻቸው ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር “ሀገሬን እገነባለሁ፣ ኃላፊነቴንም እወጣለሁኝ” በሚል ገዥ ሀሳብ እና “ወጣቶች በሀገርና በሀገረ-መንግስት ግንባታ ላይ የሚኖራቸው ሚና” በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሲያደርጉት የነበረው ውይይት የማጠቃለያ መረሀ-ግብር መሆኑን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አረጋግጧል ።

ዋፋ ማርኬቲንግና ፕሮሞሽን ፣ወጣቶች በዘላቂ የሀገር ግንባታ ሂደት ውስጥ የሚኖራቸውን አይተኬ ሚናን በጽኑ ስለሚገነዘብ የውይይት መድረኩ” አሳታፊና ለሀገር ግንባታ የሚበጁ ሀሳቦች ወደ ፊት መጥተው እንዲደመጡ ለማስቻል የድርሻውን ኃላፊነት በብቃት እየተወጣም ነው።

ዋፋ ማርኬቲንግ፣ ዓለም በኹነት ዝግጅት ዘርፍ የደረሰባቸውን አሁናዊ የቴክኖሎጂ ግብአቶች፤ ከሰለጠኑ ብቁ የተቋሙ ባለሙያዎች ጋር በማዋሀድም ጭምር ይህንን ሀገር አቀፍ የወጣቶች የማጠቃለያያ የውይይት መድረክ “ልማትና ሰላምን ለማጽናት” በሚያስችል አግባብ እየመራ ነውም።

በዚህኛው ዙር የማጠቃለያ መረሀ-ግብር” ለሰላም መጽናትና ለዘላቂ ልማት መረጋገጥ” የላቀ ፋይዳ ያላቸው አካታች የመፍትሄ ሀሳቦችና የጋራ አቋሞች የሚያዙ ይሆናልም ተብሎ ይጠበቃል።

በውይይት መድረኩ ላይ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች፣ ከመላው የሀገራችን ክልሎች የተወጣጡ ወጣቶች፣ የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች፣ምሁራን እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችም በመሳተፍ ላይ ናቸው።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top