ዋፋ ማርኬቲንግና ፕሮሞሽን ከኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የተሻሻለውን የኢትዮጵያ የንግድ ህግና የአፍሪካ ቀጠናዊ ነጻ ገበያ ስምምነትን መነሻ በማድረግ በተለይ ኢንቨስትመንትን ወደ ሃገር ለመሳብ ብሎም ሃገራዊ ለሆነ የጋራ ግብ ተቀናጅቶ ለመስራት በሚያስችል ሁኔታ ላይ ያተኮረ ውይይት እያካሄደ ይገኛል።wafaadmin | Posted on June 1, 2022 | በውይይቱ ላይ በኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በፖለቲካና ኢኮኖሚ ሚኒስትር ዴኤታ ጽ/ቤት፣ የኢኮኖሚ ዳይሬክተር ጄኔራል የሆኑት ክቡር አምባሳደር አባቢ ደምሴ፣ የዋፋ ማርኬቲንግና ፕሮሞሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ፋንታዬ ጌታነህ፣ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የንግድ ግንኙነትና ድርድር ዳይሬክተር ጄኔራል የሆኑት አቶ ሙሴ ምንዳዬ እና የኢፌዴሪ ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የሕግ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ፍሬው ማሞ እንዲሁም በርካታ የግል ባለሀብቶችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል ። ግንቦት 24, 2014 ዓ.ም Please follow and like us: Post Navigation ← Previous Post