ዋፋ ማርኬቲንግና ፕሮሞሽን ከብልጽግና ጽ/ቤት የምሥጋናና የእዉቅና ሰርተፍኬት ተሰጠው፡፡

ዋፋ የብልጽግና ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት ህንፃ ግንባታ ፕሮጀክት ሥራ ላይ ለነበረው ሁለንተናዊ አስተዋጽኦ ነው ሽልማቱ የተበረከተለት
በዝግጅቱ ላይ ዋፋን ጨምሮ እዉቅና የተሰጣቸው የተለያዩ ተቋማት፣ ባለሀብቶች ፣ አመራሮች እና ሌሎችም ተገኝተዋል።
ፕሮጀክቱ በርካታ አካላት የተሣተፉበት እሴቱም የመላው ኢትጵያውያን የሆነ የጋራ ተቋም ነዉ ሲሉ የብልጽግና ፓርቲ የዓለም አቀፍና የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሚኒስትር ዶክተር ቢቂላ ሁሪሶ በፕሮግራሙ ላይ ተናግረዋል፡፡
የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የፓርቲዉ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ በፕሮጀክቱ የተሳተፉትን ሁሉ አመስግነዋል።
ሀገርና ተቋም በትብብርና በትዉልድ ቅብብል ይገነባል ያሉት ምክትል ፕሬዝዳንቱ አዎንታዊ አስተሳሰብን ማዳበር በጭፍን መደገፍም መቃወምም ሳይሆን ሚዛናዊ መሆን ነው ፣ ብልጽግናም አፍርሶ መገንባትን ሣይሆን ሪፎርምን መርጦ በመሄዱ በርካታ ውጤት አስመዝግቧል ብለዋል።
ከሳምንታት በፊት የብልጽግና ዋና ጽ/ቤት ህንፃን የምርቃት ስነ-ስርዓት ዋፋ ማርኬቲንግና ፕሮሞሽን በደማቅ ሁኔታ ማስተባበሩ የሚታወስ ነው፡፡

መጋቢት 23,2014 ዓ.ም

Please follow and like us:
Follow by Email
YouTube
YouTube
LinkedIn
LinkedIn
Share