ዋፋ ማርኬቲንግና ፕሮሞሽን ታላቅ ሁነት እያስተባበረ ነው፡፡

በአዲስ አበባ ኅብረት ሥራ ማኅበራት ኤጀንሲ አሰናጅነት በዋፋ ማርኬቲንግና ፕሮሞሽን አስተባባሪነት የተዘጋጀው ልዩ ኤግዚቢሽን ነገ ግንቦት 18/2014 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ይከፈታል፡፡ በኤግዚቢሽኑ 200 የሚደርሱ የኅብረት ሥራ ማኅበራት ምርትና አገልግሎታቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን ከእነዚህ በቁጥር 22 የሚሆኑት ከሌሎች ክልሎች የተጋበዙ የኅብረት ሥራ ማኅበራት ሲሆኑ ቀሪዎቹ በአዲስ አበባ ከተማ ካሉ ሁሉም ክፍለ ከተሞች ሁሉም ወረዳዎች የተውጣጡ የኅብረት ሥራ ማኅበራት ናቸው፡፡ እስከ ግንቦት 21/2014 በሚዘልቀው በዚህ ኤግዚቢሽን የፋብሪካ ምርቶች፣ የግብርና ውጤቶች፣ የተቀነባበሩ ምግቦችና መጠጦችን ጨምሮ ሌሎችም ምርትና አገልግሎቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ይቀርቡበታል፡፡ ይህን ታላቅ ከተማ አቀፍ ሁነት ዋፋ ማኬቲንግና ፕሮሞሽን በድምቀት እያስተባበረው የሚገኝ ሲሆን ሁነቱ ከኤግዚቢሽን በተጨማሪ ልዩ ልዩ የመዝናኛ አቅርቦቶችንም ያጠቃለለ ነው፡፡

ግንቦት 17,2014 ዓ.ም

Please follow and like us:
Follow by Email
YouTube
YouTube
LinkedIn
LinkedIn
Share