ዋፋ ማርኬቲንግና ፕሮሞሽን “ሴት አመራሮች ለኢትዮጵያ ብልጽግና “መረሀ-ግብርን በሚፈለገው አግባብ አስተባብሮ አስፈጽሟል::

የኢፌዴሪ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ያዘጋጀውን “ሴት አመራሮች ለኢትዮጵያ ብልጽግና” መረሀ-ግብርን ሙሉ ዝግጅት፤ ዋፋ ማርኬቲንግና ፕሮሞሽን ሴቶች በሁሉም መስክ ያላቸውን ሀገር አቀፍ አስተዋጽኦ የሚያሳዩ መረሀ-ግብሮችን አካቶ በድንቅ ብቃት አስተባብሮ አስፈጽሟል።

ዋፋ ማርኬቲንግ በመረሀ-ግብሩ ላይ ፣ልዩ ልዩ በየደረጃው ያሉ ሴቶችን ተምሳሌታዊ አስተዋጽኦ የሚያሳዩ ዶክመንተሪዎች፣አስተማሪ አጫጭር የቪዲዮ ስራዎች፣ግጥሞች፣ጥዑመ ዜማዎች፣ ልዩ ልዩ ኪነጥበባዊና ስነጥበባዊ ስራዎች፣ የሞሽን ግራፒክስ ውጤቶችን ጨምሮ የሴቶችን ሀገራዊ አስተዋጽኦ የሚያሳይ መጽሄት አዘጋጅቶ ለመረሀ-ግብሩ ተሳታፊዎች ተደራሽ እንዲሆን አድርጓል ።

ይህ በንዲህ እንዳለ ዋፋ፣በሴቶች ተጠቃሚነትና ተሳትፎ ላይ አትኩረው የሚሰሩ ፓናሊስቶችን በመጋበዝም ጭምር በቀጣይ ሴቶች ይህንኑ አስተዋጽኦቸውን በሚያጠናክሩበት ሁኔታ ላይ የጋራ ውይይት እንዲያደርጉ አስቻይ ሁኔታዎችን አመቻችቷል።

ዋፋ ሙሉ ዝግጅቱን ባስተባበረው “ሴት አመራሮች ለኢትዮጵያ ብልጽና”መረሀ-ግብር ላይ በምክትል ጠቅላይ ምንስትር ማዕረግ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንትና የዴሞክራሲ ስርዓት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ፣የኢፌዴሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ምንስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ ዶ/ር ፣የጠቅላይ ምንስትር ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ዓለምጻሀይ ፓውሎስ፣የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ሎሚ ባዶን ጨምሮ ልዩ ልዩ የሴት አደረጃጀቶች ተገኝተዋል ።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top