ዋፋ ማርኬቲንግና ፕሮሞሽን፣ ኢትዮጵያ ባለፉት 9 ወራት 84 ገደማ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎችን ማስተናገድ መቻሏን አበረታች ስኬት አድርጎ ወስዷል

በሀገር አቀፍ ደረጃ ለኮንፍረንስ ቱሪዝም በመንግሥት የተሰጠውን እስትራቴጂካዊ ትኩረትን ተከትሎ አስፈላጊ መሰረተ ልማቶች፤ አዲስ አበባን ጨምሮ በክልሎች እየተገነቡ ለአገልግሎት ብቁ መደረግ መቻላቸው ዘርፉ የትኩረት ማዕከል መሆኑን በተጨባጭ የሚያሳይ ነው፡፡

ኢትዮጵያ፡ በኮንፍረንስ ቱሪዝም ዘርፍ በተጀመረው አግባብ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ሆና መውጣት እንድትችል፤ ዋፋ በዘርፉ የሀገሪቱን ዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲያዊ ተቀባይነትና ገጽታ በሚያሻሽል አግባብ የድርሻውን ኃላፊነት በብቃት እየተወጣ ያለ ወደፊትም በዚሁ ልክ የሚወጣ ስለመሆኑም ለማረጋገጥ ይወዳል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top