ከዳያስፖራው ማህበረሰብ አባላት ለህዳሴ ግድብ ከ1 ነጥብ 1 ሚሊየን ዶላር በላይ ተሰበሰበ

በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለታላቁ ህዳሴ ግድብ 1 ነጥብ 1 ሚሊየን ዶላር በላይ ተሰበሰበ፡፡

በአሜሪካ  የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከበድር ኢትዮጵያ እና ኡስታዝ ጀማል በሽር ጋር በመሆን በ’ጎ ፈንድሚ’ ሲያካሂድ የቆየው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም የማጠናቀቂያና የምስጋና መርሃ ግብር ዛሬ ተሂዷል፡፡

በመድረኩ  በ’ጎ ፈንድሚ’ ሁለት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከዳያስፖራው አባላት ለህዳሴ ግድብ 1ሚሊየን 110 ሺህ የአሜሪካ  ዶላር መሰብሰብ መቻሉን  በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ፍጹም አረጋ  ተናግረዋል፡፡

አምባሳደር  ፍጹም  ጉዳዩን አስመልክተው በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ ÷የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሙን ላስተባበሩ እና ድጋፍ ላደረጉ የዳያስፖራ አባላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ነሀሴ 20, 2013 ዓ.ም

Please follow and like us:
Follow by Email
YouTube
YouTube
LinkedIn
LinkedIn
Share