ከተማ አስተዳደሩ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የ500 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

የከተማ አስተዳደሩ አጠቃላይ በትግራይ ክልል ያለው አሁናዊ ሁኔታ እና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ በተለያዩ እርከን ካሉ የአስተዳደሩ የስራ ሀላፊዎች ጋር ምክክር አደርጓል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የመከላከያ ሰራዊት በትግራይ ክልል የነበረውን ችግር ለመቅረፍ እና የኢትዮያን ሉዓላዊነት ከማስከበር አንጻር ትልቅ ገድል ፈጽሟል ብለዋል፡፡

ለዚህ እና ለሌሎች የሀገሪቱን አንድነት እንዲሁም የህዝቡን ሰላም ለማስጠበቅ እያደረገ ላለው አበርክቶ ከተማ አስተዳደሩ 500 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉን እና በቀጣይነትም ከህዝቡ እስከ 2 ቢሊየን ብር ድጋፍ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል ነው ያሉት።

በመድረኩ የተሳተፉት እና በተለያዩ የእርከን ደረጃ ያሉት የከተማዋ አመራሮችም መከላከያ ከሽብር ቡድኑ ህወሃት የተደቀነባትን አደጋ በጀግንነት የተወጣ ታሪክ የሚያስታውሰው ተግባር መወጣቱን ተናግረዋል፡፡ (ኤፍ ቢ ሲ)

ሰኔ 29, 2013 ዓ.ም

Please follow and like us:
Follow by Email
YouTube
YouTube
LinkedIn
LinkedIn
Share