ፕሬዚዳንቱ ይህን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከቀናት በፊት በትዊተር ገጻቸው አስፍረውት የነበረውን መልዕክት በመጋራት ነው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባሰፈሩት መልዕክትም ‘’የእኛ የአፍሪካውያን ትብብር ለሁለንተናዊ እድገት ወሳኝ ነው’’ ብለዋል፡፡
በዚህም ፕሬዚዳንት ማኪ አህጉራችን ብዙ ኢኮኖሚያዊ ዕድሎች አሏት ያሉ ሲሆን÷ በትብብር ይህ እንዲሳካ ማድረግ አለብን ብለዋል፡፡(ኤፍ ቢ ሲ)