ቻይና እና ሩሲያ በቻይና መካከለኛው ሰሜን አካባቢ መጠነ ሰፊ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ እያደረጉ ነው፡፡

“ትብብር – 2021” በተሰኘው በዚህ የጋራ ልምምድ 10 ሺህ የሚደርሱ የምድር እና የአየር ሃይል አባላት ተሳትፈዋል፡፡

ሩሲያ ለልምምዱ ተዋጊ ጀቶችን፣ ሞተራይዝድ መሳሪያዎችን እና የአየር መቃወሚያ ስርዓቶችን ወደ ቻይና መላኳ ተጠቁሟል፡፡

ልምምዱ ባሳለፍነው ሰኞ ዕለት የተጀመረ ሲሆን ÷ የፊታችን ዓርብ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የጦር ልምምዱ ሽብርተኝነትን ከመከላከል እና የጋራ ደህንነትን ከማረጋገጥ ያለመ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

ከዚህ ባለፈም በሀገራቱ መካከል እየዳበረ የመጣውን ሁለንተናዊ ትብብር እና ስትራቴጂካዊ አጋርነት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያደርስ እና የሀገራቱን ቅንጅት የሚያጠናክር ነው ተብሏል፡፡ (ኤፍ ቢ ሲ)

ነሐሴ 05, 2013 ዓ.ም

Please follow and like us:
Follow by Email
YouTube
YouTube
LinkedIn
LinkedIn
Share