ትህነግ ዓለማቀፍ ድንጋጌዎችን የጣሱ ተግባራት እያከናወነ እንደሆነ ተገለጸ

ትህነግ በዓለማቀፍ ህጎች የተከለከሉ እንደ ለጦርት እድሜአቸው ያልደረሱ ህጻናትን ማሰማራት እና እነዚህ ህጻናት ባላመኑበት ጦርነት ላይ በደመ ነፍስ እንዲሰማሩ አደንዛዥ እጾችን እንደሚያቀርብላቸው ታውቋል፡፡ ለዚህም ማሳያ የሚሆነው ይህ ዘራፊ ቡድን ሲጠቀምበት የነበረ 32 ኩንታል አደንዛዥ እፅ በተሽከርካሪ ተጭኖ ከሁመራ ወደ የተለያዩ አካባቢዎች ሊገባ ሲል መያዙ ነው፡፡ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ቴዎድሮስ ብርጌድ ዋና አዛዥ ኮማንደር ዘለቀ ምትኩን ጠቅሶ አብመድ እንደዘገበው በህገወጥ መንገድ ወደ ትግራይ ሲጓጓዝ የተያዘው ይህ አደንዛዥ እፅ ካናቢስ የተሰኘ ነው፡፡

ይህንን እጽ ለጦርነት ያልደረሱ ህፃናት እንዲጠቀሙት በማድረግ ወደ ጦርነት እያስገባቸው መሆኑን እጃቸውን የሰጡ የትህነግ የልዩ ኃይል አባላት መናገራቸውን ዋና አዛዡ ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪ ህገወጡ ትህነግ በአልመዳ የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ያመረታቸው የፌዴራል ፖሊስ ፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የማረሚያ ቤት ፖሊስ አልባሳት አብሮ በቁጥጥር ስር መዋሉን ኮማንደር ዘለቀ ተናግረዋል፡፡

ህዳር 15, 2013 ዓ.ም.

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Follow by Email
YouTube
YouTube
LinkedIn
LinkedIn
Share