ተጠርጣሪዎቹ ከተለያዩ የኑሮ ዘርፎች የተውጣጡ የተለያዩ ብሔር ተወላጆች ናቸው

ግጭቶችን በማነሳሳት እና በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሽብር ጥቃቶችን በማካሄድ ተልዕኮ በሕወሃት ተላላኪነት የተጠረጠሩ ግለሰቦች በፌደራል እና በአዲስ አበባ ፖሊስ በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ከተለያዩ የኑሮ ዘርፎች የተውጣጡ የተለያዩ ብሔር ተወላጆች ናቸው፡፡ በቁጥጥር ስር የዋሉት ተጠርጣሪዎች ጠቅላላ ቁጥር ወደ 150 አካባቢ ነው፡፡ ከነዚህ ተጠርጣሪዎች መካከል ጥቂቶቹ በዋስ ተለቀዋል፡፡

እንደ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ ብዙ ድርጅቶች እና ግለሰቦች በተሳሳተ መንገድ የእስረኞችን ቁጥር በተመለከተ ሙሉ በሙሉ ያልተረጋገጠ እና የተጋነነ መረጃ እያሰራጩ ይገኛሉ፡፡ የሕግ አስከባሪያችን አሠራር ደንብን የተከተለ እንጂ እንደሚወራው በማንነት ላይ ተመስርቶ ግለሰቦችን የሚያጠቃ አይደለም የሚል መግለጫ መስጠታቸውን አብመድ ዘግቧል፡፡

ህዳር 3, 2013 ዓ.ም.

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Follow by Email
YouTube
YouTube
LinkedIn
LinkedIn
Share